1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ስምምነት የህዝብ አስተያየት

ሰኞ፣ ኅዳር 23 2017

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) መካከል የሰላም ስምምነት ላይ ተደርሷል ሲል የኦሮሚያ ክልልዊ መንግስት ትናንት አስታውቋል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ “መንግስት ከጦሩ የወጡ ግለሰቦች ጋር ያደረገውን ስምምነት ከኦነሰ ጋር ስምምነት እንዳደረገ አድርጎ ማቅረቡ አግባብነት የለውም” ሲል ተችቷል።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ማዕከላዊ እዝ ሃላፊ ሰኚ ነጋሳ ጋር
የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ማዕከላዊ እዝ ሃላፊ ሰኚ ነጋሳ ጋርምስል Oromia communication

መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ደረሱበት ስለተባለው የሰላም ስምምነት የህዝብ አስተያየት

This browser does not support the audio element.

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና በኦሮሞ  ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) መካከል የሰላም ስምምነት ላይ ተደርሷል ሲል የኦሮሚያ ክልልዊ መንግስት ትናንት አስታውቋል፡፡ትናንት በክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በኩል በተሰራጨው መግለጫው “የታጣቂ ቡድኑ ተወካይ አቶ ሰኚ ነጋሳ በታጣቂዎች በኩል ቀርበው ስምምነቱን ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ተወካይ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን ፈረሙ” ከማለት ውጪ አቶ ሰኚ በክልሉ የሚንቀሳቀሱትን ሸማቂዎች በአጠቃላይ ይወክሉ እንደሆነ በግልጽ የተብራራ ነገር የለም፡፡የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር ጋር የተደረሰ ስምምነት

ትናንት እሁድ ተደረገ የተባለው የሰላም ስምምነቱ ከአዲስ አበባ በታወጀ በሰዓታት ልዩነት፤ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ-ኦነሰ) ባወጣው ይፋዊ መግለጫ “መንግስት ከጦሩ የወጡ ግለሰቦች ጋር ያደረገውን ስምምነት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ስምምነት እንዳደረገ አድርጎ ማቅረቡ አግባብነት የለውም” ሲል የመንግስትን መግለጫ ተችቷል፡፡


ትናንት ተፈጸመ የተባለውን የታጣቂዎች እና መንግስት ሰላማዊ ስምምነት መፈረምን ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ጅሬኛ ጉደታ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አጭር ቃለመጠይቅም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የወል አመራር ተደረገ ስለተባለው የሰላም ስምምነት ምንም መረጃ እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡ያልሰመረው የመንግስት እና የኦነግ-ኦነሰ ድርድር

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተወካይ ጋር ምስል Oromia communication

“የኦነግ-ኦነሰ ተወካይ ከመንግስት ጋር የተነጋገረው ምንም ነገር የለም፡፡ የወል ከፍተኛ አመራርም ስለዚህ የሚያውቀው ነገር የለም” ብለዋል።
ስለትናንትቱ ስምምነት አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ጉዳዩ በእጅጉ የሚሳስባቸው የክልሉ ነዋሪዎችም የተደበላለቀ ስሜት የተንፀባረቀበት አስተያየት ነው የሰጡት፡፡ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW