1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ተሰናባቿ እና አዲሱ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንቶች የሕዝብ አሰተያየት

ሥዩም ጌቱ
ማክሰኞ፣ መስከረም 28 2017

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በትናንትናው እለት በቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር እና ዲፕሎማት ታዬ አጽቀስላሴ ተተክተዋል ፡፡ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያውያን በብዙ መልኩ እየታወሱ ነው?

Äthiopien Addis Abeba
ምስል Seyoum Getu/DW

ተሰናባቿና አዲሱ ፕሬዚደንቶች በምን ይታወሳሉ?

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያን  ላለፉት ስድስት ዓመታት በርዕሰ ብሔርነት ያገለገሉት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በትናንትናው እለት በቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር እና ዲፕሎማት ታዬ አጽቀስላሴ ተተክተዋል ፡፡

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያውያን በብዙ መልኩ እየታወሱ ነው?  በሳቸው የፕሬዝዳንትነት ዘመን አገሪቱ ሰፊ የሆነ አስከፊ ጦርነት ውስጥ መክረሟ ይነሳል ።

የቀድሞዋ ፕሬዚደንት ችግሮቹን የመፍታት ሚናቸው አነስተኛ እንደነበር የሚያነሱ በርካቶ ችናቸው፥ አብዛኛው ጥያቄ ጠቅላ ሚንሥትሩ ጫንቃ ላይ እንጂ ፕሬዚደንት ላይ አይደለም ያሉ አሉ ።

አዲሱ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴም ቢሆኑ አሁን በአገሪቱ የተንሰራፋው ግጭት መልክ እንዲይዝ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ሲሉ አስተያየታቸውን የሚገልጹም በርካቶችናቸው ፡፡ የአዲስ አበባ ወኪላችን አስተያየቶቹን አሰባስቧል ።

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW