1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ኢትዮ-ኤርትራ ግጭት መግለጫ እና የተቃዋሚዎች አስተያየት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 7 2008

የኢትዮጵያ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኤርትራ ኃይሎች ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ ይዞታዎች ላይ በመተኮሳቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች የአፀፋ እርምጃ መውሰዳቸውን ተናግረዋል ።

Äthiopien Minister Getachew Reda
ምስል DW/G. Tedla

[No title]

This browser does not support the audio element.



የኢትዮጵያ ጦር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኤርትራ ላይ ጥቃት የሰነዘረው ከኤርትራ ኃይሎች በኩል በደረሰበት ትንኮሳ መሆኑን ኢትዮጵያ ዛሬ አስታወቀች ።የኢትዮጵያ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኤርትራ ኃይሎች ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ ይዞታዎች ላይ በመተኮሳቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች የአፀፋ እርምጃ መውሰዳቸውን ተናግረዋል ።የኢትዮጵያ መንግሥት ለኤርትራ ትንኮሳ በአፀፋው ተመጣጣኝ እርምጃ ወስጃለሁ ማለቱን ተቃዋሚዎች የትኩረት አቅጣጫን ማስቀየሪያ ሲሉ አጣጣሉ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ዋና ዋና የሚባሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግጭቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት በሕዝብ እና በሀገር ሉዓላዊነት ላይ መቀለድ ነው የተያዘው ሲሉ ተችተዋል። አንዳንዶቹ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለዉ ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሃሳብ አቅርበዋል።ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል ።ተቃዋሚዎችን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሕርም ዝርዝር አለው።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሕር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW