1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ካቢኔ አባላት አስተያየት ከአማራ ክልል

ረቡዕ፣ መስከረም 26 2014

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት አባላትን ያካተተ ካቢኔያቸውን አቋቁመዋል። የዘንድሮው የካቢኔ አባላት ሰብጥር ሌሎች የፖለቲካ ድርጅት አባላትን ማካተቱ መልካም ጅምር መሆኑን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

Äthiopien | Bahir Dar
ምስል DW/A. Mekonnen

አስተያየት ከባሕር ዳር ከተማ

This browser does not support the audio element.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት አባላትን ያካተተ ካቢኔያቸውን አቋቁመዋል። የዘንድሮው የካቢኔ አባላት ሰብጥር ሌሎች የፖለቲካ ድርጅት አባላትን ማካተቱ መልካም ጅምር መሆኑን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ሰጥተዋል። አንዳንዶቹ በምደባው ብዙ አዳዲስ ፊቶችን አላየንምሲሉ ሌሎች ደግሞ የሴቶች ተዋፅኦ ከክልሎች የተሸለ ቢሆንም አሁንም ይቀራል ባዮች ናቸው፣ አንዳንድ ምደባዎች ደግሞ የትምህርት ዳራን ያላማዕከሉ ናቸው ሲሉ ተችተዋል። በተለይ ትምህርትና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሮች ከሙያቸው ጋር የተቀራረበ ምደባ ሊደረግላቸው ይገባ እንደነበር ተናግረዋል። አስተያቶቹን የባህር ዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን አሰባስቧቸዋል።
ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW