ስለ ደቡብ አፍሪቃው «የሰላም ንግግር» ምን ይታወቃል?
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 15 2015ማስታወቂያ
በሰሜን ኢትዮጵያ ለዓመታት ሲፋለሙ የቆዩት የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ተወካዮች «የሰላም ንግግር» ደቡብ አፍሪቃ፤ ፕሪቶሪያ ከተማ ውስጥ ዛሬ መጀመሩን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎዛ ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያን ጠቅሶ ዘግቧል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይላት ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ያደርጉታል ስለተባለው «የሰለም ንግግር» ብዙም የወጡ መረጃዎች የሉም። ሆኖም ዶይቸ ቬለ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ያንን በተመለከተ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከባልደረባዬ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ጋር ተወያይተናል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ