ስለ ዳግም ጦርነቱ የሕዝብ አስተያየት ከመቀሌ
ዓርብ፣ ነሐሴ 20 2014ማስታወቂያ
ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ውስጥ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ አራት ሰዎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጮች ገለጡ ሲል የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፦ «ሕወሓት አየር ኃይሉ ሰላማዊ ሰዎችን አጥቅቷል ለማለት እንዲመቸው በሐሰት የሰው አስክሬን የያዙ ከረጢቶችን በሲቪል መኖሪያ አካባቢዎች መጣል ጀምሯል» ማለቱን የዜና ምንጩ አክሎ ዘግቧል። የአየር ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት ዳግም ስለጀመረው ጦርነት የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ