1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ስልጠና ስለኢትዮጵያ የእጅ ጽሑፍ ድርሳነ-መዛግብት

ሐና ደምሴ
ረቡዕ፣ መስከረም 28 2018

በአዲስ አበባ ዪነቨርሰቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ሃላፊ ዶክተር ዮሐንስ አድገ የኢትዮጵያ የብዙ ዓመታት ታሪክ የተመዘገበው በጥንታዊ የሀገሪቱ ቋንቋዎች በተለይም በግዐዝ እና በአረብኛ መሆኑን፣ በነዚህ ቋንቋዎች ላይ የሚካሄድ ጥናቶችም ካለፈው ታሪካችን ለነገ የሚበጁንን ብልሀቶችን ለመቀመር የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

Äthiopien | Workshop at Goethe-Institut in Addis Ababa  
ምስል፦ Hanna Demissie/DW

ስልጠና ስለኢትዮጵያ የእጅ ጽሑፍ ድርሳነ-መዛግብት

This browser does not support the audio element.

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነልሳን እና የጥንታዊያት ድርሳናት ትምሀርት ከፍል ከጀርመኑ የሐምቡርግ ዩኒቨርስቲጋር በመተባበር ስለኢትዮጵያ የእጅ ጽሑፍ ድርሳነ-መዛግብት ለዘርፉ ምሁራን ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው ፡፡ የኢትዮጵያን ጥንታዊ መዛግብትየሚያጠኑ ምሁራንን ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እና ዳታቤዝ ላይ ከኢዮብ ሉዶልፍ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጥናትና ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር ትምህርቱ የተዘጋጀው በሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ አጋርነት ነው ፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ በኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ደርሳነ መዛገብት የእጅ ጽሑፍ ጥናቶችን ለማጠናከር እና ተቋማዊ ትብብርን ማጎልበት ነው። ኢትዮጵያ ያላት  የብዙ ዓመታት ታሪክ  ተመዝግቦ የሚገኘው በጥንታዊ የሀገሪቱ ቋንቋዎች በተለይ በግዐዝ እና በአረብኛ ነው። የአገሪቱን የሺህ ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረ  ታሪክ የጽሑፍ ቅርስ-በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግእዝ ብቻ ሳይሆን በአረብኛ እና በአጃሚም (Arabic and Ajami.) ጭምር ላይ የሚደረግ ጥናታዊ ስራ በተጠናከር መልኩ እየተሰራ እንደሆነ ለ ዶቼቬሌ የተናገሩት ዶክተር ዪሀንስ አድገ  በአዲስ አበባ ዪነቨርሰቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ኢኒስቲትዩት ዳይሪክተር ናቸው ። 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነልሳን እና የጥንታዊያት ድርሳናት ትምሀርት ከፍል ከሐምቡርግ ዪንቨስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የስልጠና መርሃ ግብር ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በተጨማሪ የአዲግራት ፣ የጎንደር ፣ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፊሰሮች እና ሌሎች ባለሙያዎችም ተካፍለዋል ።ምስል፦ Hanna Demissie/DW

አክለውም የትላንቱን በትክክል ለመርዳት የምንችለው እነኝህን ድርሳነ መዛግብት በሚገባ የሚረዳ እና የሚያጠና ምሁር በትክክል በማብቃት ብቻ ሳይሆን  መዛግብቱን ማዘመን ስንችል ነው ብለዋል  ዶ/ር ዮሀንስ ። በአዲስ አበባ  በጎተ ኢንስቲትዩት በያዝነው ሳምንት እየተካሄደ ያለው ይህ ፕሮግራም ከጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር 2016 ጀምሮ በየግዜው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዘርፉ ያሉትን የተለያዩ ጥናቶች፣ ተግዳሮቶች እና ተስፋዎች እንደዚሁም በኢትዮጵያውያን የእጅ ጽሑፍ ጥናቶችን ለማጠናከር እና ተቋማዊ ትብብርን ለመጎልበት ትልቅ ድርሻ አለው ተብሏል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነልሳን እና የጥንታዊያት ድርሳናት ትምሀርት ከፍል ከሐምቡርግ ዪንቨስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የስልጠና መርሃ ግብር ላይከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በተጨማሪ የአዲግራት ፣ የጎንደር ፣ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፊሰሮች እና ሌሎች ባለሙያዎችም ተካፍለዋል ።

ሀና ደምሴ

ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ

ፀሐይ ጫኔ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW