1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስምምነቱ እና የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሥራ እንቅስቃሴ

ረቡዕ፣ ጥር 1 2016

ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት የሚያስችላትን እድል ያገኘችበት ነው የተባለው ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ተቋሙ “ተልእኮውን ለማሳካት የሚያስችል እድል የተገኘበት ነው” ሲል የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ገለፀ።

Äthiopien Addis Abeba | Statement der Navy
አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ የባህር ኃይል የስራ እንቅስቃሴ ተደመጠ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሥራ እንቅስቃሴ

ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት የሚያስችላትን እድል ያገኘችበት ነው የተባለው ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ተቋሙ “ተልእኮውን ለማሳካት የሚያስችል እድል የተገኘበት ነው” ሲል የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ገለፀ። 

በ2011 ዓ. ም በአዋጅ እንደገና የተቋቋመው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል 4 የቀድሞ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል መኮንኖች እያማከሩት፣ በፈረንሳይ ድጋፍ በሰው ኃይል ፣ በስልጠና እና በባሕር ልምምድ ራሱን ሲያደራጅ መቆየቱን ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰላም እና የወጭ ግንኙነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት አስታውቋል። 

የባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ሪል አድሚራል ናስር አባዲጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ “በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር ውኃ ላይ መንቀሳቀስ እንችላለን ብለን ሥንሠራ ቆይተናል። በቅርብ ጊዜም ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ በስምምነት ወዳገኘችው የባሕር በር ግዳጅ እንገባለን ብለን እናስባለን” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኢትዮጵያ የንግድ መርከቦቿን ከአደጋ እንድትጠብቅ እና በቀጣናው ያለውን የሕገ ወጥ የመሣሪያ እና የሰዎች ዝውውርንም ለመከላከል ይሰራል ተብሏል።

የኢትዮ - ሶማሌላንድ ስምምነት ለኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ያለው አንደምታ

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ሪል አድሚራል ናስር አባዲጋ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በቅርቡ የተፈራረሙትና ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነው ኢትዮጵያን የባሕር በር ያስገኛታል የተባለው ስምምነት ከየትም ለሚመጡ የሲቪል መርከቦች ዋሥትና እና ደኅንነት ማረጋገጫ የሚሰጥ እና ለተቋሙ “ተልእኮን ለማሳካት የሚያስችል እድል የተገኘበት ነው”ብለዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት የሚያስችላትን እድል ያገኘችበት ነው የተባለው ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ተቋሙ “ተልእኮውን ለማሳካት የሚያስችል እድል የተገኘበት ነው” ሲል የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ገለፀ። ምስል Solomon Muchie/DW

ዳግም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል 

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በኢትዮጵያ እና በብሔራዊ ጥቅሞቿ ላይ በአካባቢው ከሚገኙ የውኃ አካላት ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት ለመከላከል እና ለመመከት የሚል ተልእኮ ይዞ በ2011 ዓ. ም እንደገና የተቋቋመ ሲሆን በተለይም ኢትዮጵያ ብቸኛ የውጪ ንግድ መስመሯ የሆነው የጀቡቲ ማዕዘን እና የንግድ እንቅስቃሴዋ እስከመቼ በሌሎች ሀገሮች ይጠበቃል ለሚለው ምላሽ ለመስጠት ተቋሙ ሥራ ላይ መሆኑ እንደተገለፀላቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ፈቲሂ ማህዲ ተናግረዋል።

እየተደራጀ ያለው ባሕር ኃይሉ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ከባቢ ያለባትን የደኅንነት ሥጋትም ለመከላከል በጎረቤት ሀገራት ፣ በምእራብ አፍሪካ እና በአውሮፖ አባላቱን እና አመራሮቹን ሲያሰለጥን እና ልምድ ሲያሰባስብ መቆየቱ ለጋዜጠኞች ዝግ ሆኖ በቀረበው ሪፖርተ‍እ እንደተገለፀላቸው ተናግረዋል።

የአለምን ተኩረት የሳበው የመግባቢያ ሰነድ ፊርማአወዛጋቢው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ የመግባቢያ ሰነድ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው ቃል ዐቀባይና የውጭ እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የተስማሙበት ጉዳይ በጥብቅ ዲፕሎማሲያዊ መርህ መመራት ያለበት መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያን እና የሶማሌላንድን ስምምነት ተከትሎ አለምአቀፍ ተቋማት እና ድርጅቶች እንዲሁም ሀገራት የሶማሊያ ሉአላዊ ግዛት እንዲከበር የሚጠይቁ መግለጫዎችን አውጥተዋል። ከቀናት በፊት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ወደ ኤርትራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያይተዋል።

የባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ሪል አድሚራል ናስር አባዲጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ “በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር ውኃ ላይ መንቀሳቀስ እንችላለን ብለን ሥንሠራ ቆይተናል። በቅርብ ጊዜም ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ በስምምነት ወዳገኘችው የባሕር በር ግዳጅ እንገባለን ብለን እናስባለን” ብለዋል።ምስል Solomon Muchie/DW

በዚሁ እለት የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በወታደራዊ ጉዳይ አብረው ለመሥራት አዲስ አበባ ላይ ንግግር አድርገዋል።የኢትዮጵያና ሶማሌላንድ ዉል ከቪየናዉ ስምምነት አኳያ

የፈረሰው የቀድሞው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል 

ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1947 ማዘዣ ማዕከሉን ምፅዋ፣ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱን አስመራ ላይ ያደረገ አሰብን ያካለለና በ1950 ዓ. ም ሥራ የጀመረ ጠንካራ ባሕር ኃይል የነበራት ሲሆን ኤርትራ ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነች ማግስት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ባሕር ኃይልም ፣ ወደብ አለባም ሀገር ሆናለች። 

ይሄው ተቋም በ2011 ዓ.ም እንደገና የተቋቋመ ሲሆን እስከ 300 የሚደርሱ አባላቶች እንዳሉትም ተነግሯል። 

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW