1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ስራ ስላልመረጥኩ ነው» አማኑኤል የማታ

ዓርብ፣ ጥር 24 2005

አማኑኤል የማታ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በመንገድ ግንባታ ሥራ ተሰማርቶ የሚገኝ ወጣት ነዉ። ወጣቱ የሥራ ፍቅር እንዳለው ይናገራል።

Fotolia 7262773 vorsicht baustelle! © emmi - Fotolia.com
ምስል Fotolia/emmi

ጀርመን 650 000 ኪሜ ግድም ርዝመት ያለው መንገድ እንዳላት ይነገራል። በስፋት ከጀርመንን በሶስት እጅ በምትበልጠው በኢትዮጵያ ምንም እንኳን በርካታ መንገዶች እየተሰሩ ቢሆንም አሁንም በቂ አይደሉም። ሌሎች ተጨማሪ መንገዶችን መስራቱ ገና አመታት ሊፈጅ ይችላል። በኢትዮጵያ የመንገድ ስራ ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥሯል። አማኑኤል በዚህ የስራ መስክ ከተሰማሩት ወጣቶች አንዱ ነው። በአሁኑ ወቅት ወላይታ አካባቢ እየሰራ ይገኛል።

ምስል DW

ዛሬ የምሽት ተረኛ ነው። ከ 1992 ጀምሮ ወጣቱ በዚሁ ስራ ላይ ይገኛል። ስራው ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎችም ወስዶታል። ወጣቱ ወደዚህ ሙያ የተሰማራው ድራጋዶስ ድርጅት ውስጥ መስራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነው። ቀጣሪዎቼም በስራዬ ደስተኛ ስለነበሩ ተባበሩኝ ይላል አማኑኤል። ኋላም መንጃ ፍቃድ አወጣ። ዛሬ መኪና ብቻ ሳይሆን ሌሎች ለመንገድ ስራ የሚያገለግሉ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ያንቀሳቅሳል። አማኑኤል ስራው ፈታኝ መሆኑንም ሳይጠቅስ አላለፈም።

የቻይና የመንገድ ሰራተኞች ኢትዮጵያ ውስጥምስል AP

ከሳምንት በላይ ዕረፍት ኖረኝ መቀመጥ አልወድም ይላል አማኑኤል ። በስራውም ደስተኛ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በመንገድ ስራ ስሟ ተደጋግሞ የሚነሳው ሀገር ቻይና ናት። ሆኖም አማኑኤል ብዙ ኢትዮጵያውያን የመንገድ ስራ ተቋራጮች እንዳሉ ይናገራል።

ስራው ጥሩ ክፍያ አለው። ተግተው ከሰሩ ከ 5000-9000 ብር በወር ይገኝበታል። እንደ አማኑኤል ገለፃ።

ከአማኑኤል የማታ ጋ ያደረግነውን ሙሉ ጭውውት ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW