1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ስቶክሆልም፤ የአቶም ጦር መሳርያ ምርት እየጨመረ ነዉ

ሰኞ፣ ሰኔ 5 2015

የዓለማችን የኒውክሌር መሳሪያ ባለቤት ሃገራት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻቸውን እያጠናከሩ መሆኑን ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘዉ ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም ገለፀ። ተቋሙ ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ መግለጫ፤ በዓለም ላይ በሚገኙ በወታደራዊ ክምችቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ሊዉሉ የሚችሉ የኑክሌር የጦር መሣሪያዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት በቁጥር ጨምሯል ብሏል።

Russland, Plesetsk  | Interkontinentalrakete des Typs Yars während einer Atomübung (2022)
ምስል፦ Russian Defense Ministry Press Service/AP/picture alliance

የዓለማችን የኒውክሌር መሳሪያ ባለቤት ሃገራት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻቸውን እያጠናከሩ መሆኑን ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘዉ ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም ገለፀ። ተቋሙ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ መግለጫ እንዳስቀመጠዉ በዓለም ላይ በሚገኙ በወታደራዊ ክምችቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ሊዉሉ የሚችሉ የኑክሌር የጦር መሣሪያዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት በቁጥር ጨምሯል ብሏል። በሌላ በኩል በዋና ዋናዎቹ የኑክሌር ጦር መሳር  ባለቤት ሃገራት መካከል የሚታየዉ የመግባባት፤ የግንኙነት እና የሐሳብ የመለዋወጥ እንቅስቃሴ ከበርካታ አሥርተ ዓመታት ወዲህ በጣም ቀዝቃዛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ነዉ ሲል ተቋሙ አሳሳቢነቱን ገልጿል። ገለልተኛ የሆነዉ ስቶክሆልም ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም አደረኩት ባለዉ ግምገማ ከጎርጎረሳዉያኑ ጥር 2023 ዓ.ም ወዲህ በዓለም ሃገራት ወታደራዊ ክምችቶች ጥቅም ላይ ሊውሉ በሚችሉ 9,576 የአቶም የጦር መሣሪያዎች አሉ ሲል ግምቱን አስቀምጧል። የሰላም ተመራማሪው ተቋም ቃል በቃል እንዳስቀመጠዉ ያለንበት ጊዜ "በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ አደገኛ ከሆኑት ወቅቶች አንዱ" ነዉ ሲል ገልጿል። 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW