ስኖውደን ተሸለመ
ሐሙስ፣ መስከረም 15 2007ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስን መንግሥትን የሥለላ ሴራ በማጋለጡ ከሐገሩ ለመሰደድ የተገደደዉ የቀድሞዉ አሜሪካዊ የሥለላ ድርጅት ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖደን «አማራጭ ኖቤል» የተሰኘዉን ሽልማት አገኘ።መንበሩን ስቶክሆልም-ስዊድን ያደረገዉ ሸላሚ ድርጅት RightsLivelihood እንዳስታወቀዉ ስኖደን የተሸለመዉ በዓለም የማትደፈረዉን ሐያል ሐገር በማጋለጥ ለመናገር ነፃነት መከበር መቆሙን በማረጋገጡ ነዉ።ለወትሮዉ የተሸላሚዎች ሥም ዝርዝር በይፋ የሚነገርበት የሲዊድን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ግን መስሪያ ቤት ግን የዘንድሮ ተሸላሚዎች ስም ዝርዝር ከቢሮዉ እንዳይነገር አግዷል።
ቴዎድሮስ ምሕረቱ
ነጋሽ መሐመድ