ስደተኞችን ለመቆጣጠር የተስማማ ጉባኤ በሮም
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 18 2015
ከአፍሪቃና ከሌሎች አዳጊ ክፍለ ዓለማት ወደ አዉሮጳ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ አዉሮጳ እንዳይገቡ መግታትና ስደተኛ አሸጋጋሪዎችን መቆጣጠር በሚቻልበት ስልት ላይ የተነገራገረ ጉባኤ ባለፈዉ ዕሁድ ሮም-ኢጣሊያ ዉስጥ ተደርጓል።በጉባኤዉ ላይ ከ20 የሚበልጡ ሐገራት መሪዎች፣ ባለስልጣናትና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።ኢጣሊያ የጠራችና ያስተባበረችዉ ጉባኤ ተሳታፊዎች ሕገ-ወጥ የሚሏቸዉን ስደተኞችና የስደተኛ አሸጋጋሪዎችን ለመቆጣጠር ያስችላል ያሉትን የጋራ ዉል ተፈራርመዋል።
የእሁዱ ስብሰባ እነሱ ህገወጥ በሚሉት መንገድ ወደ አውሮፓ በሚገቡት ስደተኖችና በሚከስተው ቀውስ ዙሪያ፤ ከሜዲታርኒያን ባህር አካባቢ አገሮች ጋር በስፋት ለመምከርና የጋራ የትብብርና የትግበራ ስልት ለማዘጋጀት፤ በጠቅላይ ሚኒስተር ጆርጂያ ሜሎኒ የተጠራ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ እንደሆነ ታውቋል። በጉባኤው፤ ካደቡባዊ አውሮፓ ከፈረንሳይና ስፔን በሰተቀር፤ ቱርክን ጨምሮ ሌሎቹ አገሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የገልፍ ባህረሰልጤ አገሮች፣ የስሜን አፍሪካና ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የምስራቅ አፍርካ አገሮች መሪዎች በስብስባው ተገንተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒ በስብሰባው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ የሰዎች ህገወጥ ዝውውርና ፍልሰት ማንንም የማይጠቅም መሆኑን አንስተው፤ የፈላሲይንና ስደተኖች መነሻዎች፤ መተላለፊያዎችና መዳረሻ የሆኑ አገሮች በችግሩ ዙሪያ ተወይተው የጋራ መፍትሄ መፈለግ ያለባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል። ‘ ‘ “ “በገፍ የሚደረግ ህገወጥ የሰዎች ፍልሰት ሁላችንንም ነው የሚጎዳው። ከዚህ የሚጠቀሙት የሰው አዘዋዋሪ ነግዴዎች ብቻ ናቸው” በማለት የነዚህ ወንጀለኖች ድርጊት ዜጎችን ለአደጋ የሚያጋልጥ፤ መንግስታትን ለኢኮኖሚና ለፖለቲክ ቀውስ የሚዳርግ መሆኑን አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ በመቀጠልም፤ “ ይህ ጉባኤ የእኩያሞች ስብስብና በመከባበር ላይ ውይይት የሚያደረግበት ጉባኤ ነው” በማለት በአውርፓና በሌሎቹ የሜዲትራኒያን ባህር አዋሳኝ አገሮች መክከል ያለው ግንኙነት የፉክክርና የጥቅም ግጭቶች የሚስተዋልበት ሳይሆን፤ በጋራ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ላይ የተመሰረተ የዕኩሎች ግንንኙነት መሆን እንዳለበት አጽኖት ሰተው ተናግረዋል።
የአውሮፓ ኮሚሺን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ቮንዴርሌየን በበኩላቸው ባሰሙት ንግግር ፤ግዜው አዳዲስ ተግዳሮቶች የሚስተዋሉበት መሆኑን አንስተዋል፤ “ በተለየ ግዜና ሁኔታ ላይ ነው የተገናኘነው። የአየር ለውጥ ችግር አግጦ ወቷል። ሁላችንም ወደ ንጽህ የሀይል አቅርቦት መዞርና አዳዲስ የግብርና ቴክኒኮችን በስራ ላይ መዋል ይኖርብናል፤ የሰው ሀይላችንንም ወቅቱ በሚፈልገው መጠን ማሰልጠን ይገባናል” በማለት የአየር ለውጥ ከፍተኛ ተግዳሮት ይዞ የመጣ ቢሆንም አዳዲስ ዕድሎችም ያሉት መሆኑን ጠቀሰዋል። በሰዎች ስቃይ የሚበልጸጉትን የሰው አዘዋዋሪ ወንጀሎችን ማስቆም፤ በሜድትራኒያን ባህር ላይ የሚደርሰውን የሞት አደጋ ማስቀረት፤ አጣዳፊ ተግባር መሆን እንዳለበት ያወሱት ወይዘሮ ቮንዴርሌየን፤ ይህ ሁሉ ግን አሉ “ ይህ ሁሉ በሜድትራኒያን ባህር አካባቢ ያሉ አገሮች አዲስ አስተሳሰብ መንገባትና አዳዲስ የትብብር ማዕቀፎችን መዘርጋት የሚገባቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡ በንግድ፤ በኢንቨስትሜንት፤ በስደተኖች ላይ፤፣ ሉኡላዊንትንና የጋራ ሀላፊነትን መሰረት ያደረገ አዲስ አይነት ትብብር ማድረግን ይጠይቃል ሲሉ፤ ከጉባኤተኞች የሚጠበቀውን ሀላፊነትና ግዴታ አስረድተዋል።
መሪዎቹ በመጨረሻም በአንድ ቀን ሙሉ ውይይታቸው፤ ሰዎች የሚፈናቀሉባቸውንና የሚሰደዱባቸውን መሰረታዊ ምክኒያቶች ለመለየትና በነሱም ላይ ለመስራት፤ በሜድትራኒያን አካባቢ ባሉ አገሮች የሚንቀሳቀሱ የሰው አዘዋዋሪ ወንጀሎችን ለማስወገድ የሚያስችል “የሮም ፕሮሴሰ” የተሰኘ የጋራ ስምምነት አጽድቀዋል። በስምምነቱ የተጠቀሱትን ተግዳሮች ለመቋቋምና ውጤት ለማስመዝገብ ተስብስባዎቹ በማህበራዊና ኢኮኖሚ እድገት፤ በድህነት ቅነስ፤ በስው ሀይል ስልጠናና የስራ ፍጠራ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ለማድረግ የተስማሙ መሆኑም በሰነዱ ተገልጿል። በዲሱ የሮም የስምምነት ሰነድ መሰረት ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስፈልገውን ገንዘብ፤ ከለማቀፍ የገንዘብ ድርጅቶችና ከለጋሽ አገሮች ለማግኘት የታሰበ ሲሆን፤ ለግዜውው ከተባበሩት አረብ ኤሚሪቶች 100 ሚሊዮን ኢሮ እንደተለገሰና ወደፊት ግን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕርግራም እንደሚዘጋጅ ወይዘሮ ሜሎኒ በስብሰባው መዝጊያ አስታውቀዋል።
ይህ ጉባኤና ጉባኤተኖቹ የደረሱበት ስምምነት የፈላስያንን ቁጥር የሚቀንስ፤ በስደተኖች ላይ የሚደርሰውን እንግልትና ሞት የሚያስቀር መሆኑን ግን በተለይ የስደተኖች ድርጅቶችና የሰባዊ መብት ተክራክራዎች አብዝተው ይጠራጠራሉ።
ገበያው ንጉሤ
ነጋሽ መሐመድ
ታምራት ዲንሳ