1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞችን ከዳዳብ ወደ ሶማሊያ ለመመለስ መታቀዱ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 18 2005

ከዓለም ትልቁ የስደተኞች መጠለያ የኬንያው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ ነው ። ዳዳብ ከ20 ዓመት በፊት ከሶማሊያ የተሰደዱ ና ከዚያም በኋላ የሄዱ የተጠለሉበት ስፍራ ነው። ከስደተኞቹም አንዳንዶቹ እዚያው የተወለዱ ናቸው ።

Flüchtlingslager Dadaab Keniaምስል AP

የኬንያ መንግሥት አሁን የሶማሊያ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ይፈልጋል ። ብዙዎቹ ግን ለዚህ አልተዘጋጁም ። ዳዳብ በሚገኘው ከዓለም ትልቁ የስደተኞች መጠለያ ቁጥራቸው ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሰዎች በአነስተኛ ጎጆዎችና በድንኳኖች ይኖራሉ ። አብዛናዎቹ ከ20 ዓመት በላይ ጦርነት ወደተካሄደባት ሃገራቸው መመለስ አይፈልጉም ። ከዓለም ትልቁ የስደተኞች መጠለያ የኬንያው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ ነው ። ዳዳብ ከ20 ዓመት በፊት ከሶማሊያ የተሰደዱ ና ከዚያም በኋላ የሄዱ የተጠለሉባት ስፍራ ናት ። ከስደተኞቹም አንዳንዶቹ እዚያው የተወለዱ ናቸው ። የኬንያ መንግሥት አሁን የሶማሊያ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ይፈልጋል ። ብዙዎቹ ግን ለዚህ አልተዘጋጁም ። ዳዳብ የሚገኘው ከዓለም ትልቁ የስደተኞች መጠለያ አብዛኛው ክፍል እንደ ከተማ የሚቆጠር ነው ። በመጠለያው የፍራፍሬና የጥራጥሬ ገበያ፣ አነስተኛ ሱቆች ይገኛሉ ። የስልክ ካርዶች ባትሪ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ሳይቀሩ ይሸጣሉ ። ከ20 ዓመት በፊት በተመሰረተው በዚህ መጠለያ ቁጥራቸው ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሰዎች በአነስተኛ ጎጆዎችና በድንኳኖች ይኖራሉ ። ከ20 ዓመት በላይ ጦርነት ወደተካሄደባት ሃገራቸው መመለስ አይፈልጉም ።ከስደተኞች አንዳንዶቹ እዚያው ነው የተወለዱት ።«ወደ መጠለያው የመጣሁት የአንድ ዓመት ልጅ ሳለሁ ነበር ።አሁን 23 ዓመቴ ነው »ብዙዎቹ ወደ መጠለያ የጎረፉት የዛሬ 2 ዓመት በሶማሊያ በተከሰተው ድርቅና ረሃብ ምክንያት ነበር ።

ምስል WFP/Rose Ogola7/picture alliance/dpa

ከዚያን ጊዜ አንስቶ ዳዳብ በስደተኞች እንደተጨናነቀች ነው ። ለኬንያ መንግሥት መጠለያው ዓይን እንደሚጎዳ እሾህ ነው የሚታየው ። መንግሥት መጠለያው በቋሚነት እንዲቀጥል አይፈልግም ። ስደተኖቹ ከሚቀጥለው ወር አንስቶ ወደ ሶማሊያ መመለስ አለባቸው ይላል ። በዚህ ጉዳይ ላይ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የሶማሊያው አቻቸው ሃሰን ሼክ መሐመድ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ተነጋግረው ነበር ። ኬንያ ስደተኞችን ከማስጠለል ይልቅ የሶማሊያው የሰላም ሂደት መደገፍ ነው የምትመርጠው ። ኡሁሩ ኬንያታ በዚህ ረገድ የመንግሥታትን ትብብር ጠይቀዋል ። « የሁለታችንም መንግሥታት በተገቢው መንገድ መርሃ ግብሩን ተግባራዊ ማድረግ እንድንችል ወዳጅ መንግሥታት አብረውን እንዲሰሩ ጥሬ እናቀርባለን ። የአሸባብ ርዝራዦችን ተከታትሎ ለማደን ፣ ደህንነት የማስጠበቅ ዘመቻችን ፣ የመረጃ ልውውጥን የሚያጠናክር መሆን ይገባዋል ። »ፅንፈኞቹ ሙስሊም ሚሊሽያዎች ከረዥም ጊዜያት አንስቶ አብዛኛውን የሶማሊያ ክፍል ይቆጣጠራሉ ። ሚሊሽያዎቹ ከ2 ዓመት በፊት በአፍሪቃ ህብረት ኃይሎች ከሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሾ ቢባረሩም በሽምቅ ውጊያ የሚያደርሱት ጥቃት እንደቀጠለ ነው ።

ምስል picture alliance/dpa

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ አሸባብ መቅዲሾ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ቢሮ ላይ ጥቃት አድርሷል ። ይሁን እንጂ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች በሶማሊያ ሁኔታው ፍፁም ተስፋ አስቆራጭ ነው አይሉም ። ተስፋ የተጣለው ከሁሉም በላይ በዚህ ዓመት መግባያ ላይ ሥልጣን በያዘው በአዲሱ የሶማሊያ መንግሥት ላይ ነው ። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ መሐመድ በሶማሊያ የበለጠ ሰላም ያሰፍናሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል ።ፕሬዝዳንት መሐመድ ሰዎቹን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ተዘጋጅተዋል ።« እነዚህ ስደተኞች ወደ የመንደሮቻቸው ወደ ሃገራቸው ፣ ሶማሊያ ወደ ሚገኙ ቤታቸው እንዲመመለሱ ማረጋገጥ አለብን ። »አብዛኛዎቹ ሶማሌዎች ግን ሁኔታውን በተለየ መንገድ ነው የሚመለከቱት ። ዳዳብ ለሚገኙ ወጣቶች ሶማሊያ ከአሁን በኋላ ሃገራቸው አይደለችም ። አብዛኛዎቹ ሶማሊያን አያውቁም ፤ የሶማሊያ ምንም ትውስታም የላቸውም ።

ምስል picture alliance/dpa/WFP/Rose Ogola

« ወደ ዚህ ስመጣ በጣም ልጅ ነበርኩ ። በእናቴ ጀርባ ታዝዮ ነው የመጣሁት ። አሁን ለኛ ጥሩ የመመለሻ ጊዜ አይደለም ። እዚያ ብንሄድ ብዙ የሚገጥሙን ነገሮች አሉ ። ልንደፈር ልንገደል እንችላለን »« ሶማሊያን አይቻት አላውቅም ። አሁን ወደ እዚያ ብመለስ ፍጹም ባዕድ ነው የምሆነው »ይሁንና መንግሥት ይህን የስደተኞቹን ስሜት እምብዛም ከግምት ውስጥ ማስገባት የሚፈልግ አይመስልም ። የፊታችን ነሐሴ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ የሶማሊያ ጉባኤ ለማካሄድ ታቅዷል ። በዚህ ጉባኤ ላይም ስደተኞቹን ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበት ዝርዝር ሁኔታ ይመከርበታል ። በኬንያ መንግሥት እቅድ የጎርጎሮሳውያኑ 2013 ዓመተ ምህረት ከመጠናቀቁ በፊት ከስደተኞቹ አብዛኛዎቹ ወደ ሃገራቸው መመለስ አለባቸው ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW