ስደተኞች እና በ«ዩሮታነል» የተፈጠረው ውዝግብ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 23 2007ማስታወቂያ
በዚሁ ሙከራ ትናንት አንድ የሱዳን ዜጋ የሆነ ስደተኛ የጭነት ተሽከርካሪ ገጭቶት ሕይወቱ አልፋለች፣ አንድ ሌላ ደግሞ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ ባደረገው ሙከራ በደረሰበት የመቁሰል አደጋ ዛሬ መሞቱ ተሰምቶዋል። ካለፈው ጥር ወር ወዲህ ከ37,000 የሚበልጡ ስደተኞች «ዩሮታነል»ን ጥሰው ብሪታንያ ለመግባት ሙከራ አድርገዋል። የፈረንሳይን እና የብሪታንያን ባለሥልጣናት ያሳሰበውን ይህንኑ ጉዳይ ተከትሎ፣ የፈረንሳይ የሃገር አስተዳደር ሚንስቴር ትናንት በርካታ ልዩ የፖሊስ ኃይል በካሌ ከተማ አሠማርቶዋል።
ሀይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ