ስድስተኛው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫን ስለመታዘብ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 2 2013ማስታወቂያ
ስድስተኛው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትኃዊና ገለልተኛ እንዲሆን የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምርጫውን ለመታዘብ እንዲዘጋጁ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ከዚህ በፊት ምርጫዎችን እንደታዘቡ የተናገሩ ያነጋገርናቸው የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ነበረ ባሉት ምቹ ያልሆነ የፖለቲካ ምኅዳር፣ አፋኝ ሕጎችና የአቅም ማነስ ድርጅቶቹ ይህንን ትልቅ ኃላፊነት የመወጣት ሚና ነበራቸው ማለት እንደማያስደፍር ገልፀዋል። አሁንም ውጥረት የበዛበትና የሠላም እጦት የሚታይበት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ምርጫን ለመታዘብ ምቹ ባይሆንም ፣ መራጮችን በማስተማር ፣ በማንቃትና ጫና እንዳይደርስባቸው በማድረግ ሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ