1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስድስተኛው «ጣና ፎረም» በባሕርዳር ከተማ

እሑድ፣ ሚያዝያ 15 2009

ስድስተኛው ጣና ፎረም በባሕርዳር ከተማ ትናንት እና ዛሬ ተከናውኗል።  የውይይቱ ዋነኛ ትኩረት «የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር በአፍሪቃ» የሚል እንደነበር ተጠቅሷል።

Äthiopien - 6th Tana Forum in  Bahir Dar
ምስል Y. G. Egiziabher

ስድስተኛው «ጣና ፎረም» በባሕርዳር ከተማ

This browser does not support the audio element.

ስድስተኛው ጣና ፎረም በባሕርዳር ከተማ ትናንት እና ዛሬ ተከናውኗል። የውይይቱ ዋነኛ ትኩረት «የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር በአፍሪቃ» የሚል እንደነበር ተጠቅሷል። በአኅጉሪቱ የሚገኙ ሃገራት መስተጋብር እና ከቅን ዘመን አንስቶ አፍሪቃ በዓለም አቀፉ መድረክ ያላት ድርሻ ተጠቃሚነቷን ያማከለ አለመኾኑ በርካታ ችግሮችን ፈጥሯል ተብሏል። ከእነዚህም መካከል፦ ድህነት፤ ሙስና፤ ሥራ አጥነት የአካባቢ ጉስቁልና፤ ግጭት እና ብጥብጥ እንደሚጠቀሱ የጣና ፎረም በድረ-ገጽ ያወጣው ሐተታ ይዘረዝራል።

ባለፉት ስድሳ ዓመታት በአፍሪቃ ውስጣዊ የነፍጥ ግችቶች ከግማሽ በላይ ከተፈጥሮ ሀብት ጋር በተያያዘ የተከሰቱ መኾናቸውም ተጠቅሷል። ይኽ በመኾኑም አፍሪቃ በዓመት 18 ቢሊዮን ዶላር እንደምታጣ ኦክስፋም መግለጡ ተዘግቧል።

በዘንድሮው ውይይት ከዩጋንዳው ፕሬዚዳንት እና ከጠቅላይ ሚንሥትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በስተቀር የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች እንዳልተኙ ኾኖም ተወካዮቻቸውን እንደላኩ በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጦልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW