1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፔን ኮስታሪካን 7 ለ0 ድባቅ መታ

ረቡዕ፣ ኅዳር 14 2015

በቀጠር የዓለም ዋንጫ ውድድር የምድብ «ሠ» ግጥሚያ የስፔን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ኮስታሪካን የግብ ጎተራ አደረገ። በጨዋታው ፍጹም ብልጫ ያሳዩት ስፔኖች ኮስታሪካን 7 ለ0 በሆነ እጅግ ሰፊ የግብ ልዩነት የግብ ጎተራ አድርገዋል።

FIFA Fußball-WM 2022 | Spanien vs. Costa Rica | 3. Tor Spanien
ምስል Carl Recine/REUTERS

በቀጠር የዓለም ዋንጫ ውድድር የምድብ «ሠ» ግጥሚያ የስፔን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ኮስታሪካን የግብ ጎተራ አደረገ። በጨዋታው ፍጹም ብልጫ ያሳዩት ስፔኖች ኮስታሪካን 7 ለ0 በሆነ እጅግ ሰፊ የግብ ልዩነት የግብ ጎተራ አድርገዋል። መደበኛ ጨዋታው ተጠናቆ በባከነ 2 ደቂቃ ላይ 7ኛው ግብ ተቆጥሯል። እስከዛሬ በነበሩ ጨዋታዎች በርካታ ግብ የተቆጠረው በዛሬው ግጥሚያ ነው። ሰኞ ዕለት በነበረው ግጥሚያ እንግሊዝ የኢራን ቡድንን 6 ለ2 አሸንፋነበር።

ቀደም ሲል በነበረው ግጥሚያ ጃፓን ጀርመንን 2 ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። ከጃፓንና ጀርመን በፊት የተጫወቱት ሞሮኮና ክሮሽያ ዛሬ ያለምንም ግብ ተለያይተዋል። በዚህ ጨዋታ ሞሮኮ ተጋጣሚውን አስጨናቂ ቡድን መሆኑን አስመስክሯል።

በምድብ «ረ» ዛሬ ማታ ቤልጂየም ከካናዳ ይጫወታሉ። ሌሎች ጨዋታዎችም ነገ ይቀጥላሉ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW