1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት ሐምሌ 10፣2009 ዓ.ም

ሰኞ፣ ሐምሌ 10 2009

ሮጀር ፊዲሪር  እና ጋብሪ ሙግሩዛ የ2017 የዊምብልደን ሻንፒዮን ሆኑ። በታላቅዋ በብሪታንያ ሲልቭርስቶን የተካሂደው የፎርሙላ ዋን የግራንፕሪክስ ውድድር በ ሉዊስ ሀምልተን  አሽናፊነት ተጠናቀቀ። ፊፋ የ 2022 የዓለም ዋንጫ አዠጋጅ ኳዋታር የዝግጅት ፍቃድዋ ነጠቀ ሲባል የተሰራጨውን ዜና ውሸት ሲል አስተባብሏል።

Wimbledon 2017 | Finale Herren | Sieger Roger Federer
ምስል Getty Images/J. Finney

ስፖርት ሐምሌ 10፣2009 ዓ.ም

This browser does not support the audio element.

 

የኢትዮጵያ ስፖርት እና ባህል ፊደሬሽን በታላቅዋ ብሪታንያ በየዓመቱ የሚያደርገውን ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ዝግጅት በሳምንቱ ቅዳሜ እና እሁድ በመዲናይቱ  ለንደን  ዊስትህንም መታሰቢያ የስፖርት ማዘውተሪያ ሚዳ ላይ አካሂድዋል። 

በከተማው ምስራቃዊ ክፍል የተስተናገደው ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ድግስ ለሰባተኛ ጊዜ የተካሂደ ነው። ኢትዮጵ ያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለሁለት ቀናት ተሰባስበው በተለያዩ ስፖርታዊ  አዝናኝ ዝግጅቶች ላይ በጋራ አሳልፈዋል።

ምስል picture-alliance/empics/G. Fuller

የዝግጅቱ ተቀዳሚ ዓላማ በብሪታንያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሠላማዊ በሆነ መንገድ በስፖርት እና በባህል ዙሪያ ለማገናኘትና ኅብረታቸውን ለማጥናከር አንድነታቸውን ለማደርጀት ሲሆን በጤና በትምህርት በንግድ እና በተለያዩ የማኅበራዊ ዘርፎች እርስ በእርስ አንዲረዳዱ  ማንነታቸውን  እንዲያከብሩ  ብሎም በማንነታቸው  እንዲተማመኑ  ከዚህ በተጨማሪ ከሌሎች ማህበረሰብ ጋር በእኩልነት ለመኖር የሚያስችለውን ብልሃት ለመዘየድ አና ለማገዝ  መሆኑ ተነግሮአል። 

አትሌቲክስ

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማኅበር የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ የብር ሚዳልያ ባለቤት የሆነውን ፍራንኪ ፍሪድሪክን ለጊዜው ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማኅበር ማዕከል ከአባልነቱ ማገዱን ዛሪ አስታወቀ። ባለፈው መጋቢት ወር አንድ የፈረንሳይ ጋዜጣ አትሌቱ የጎርጎረሳዊ 2016 ዓ,ም የኦሎምፒክ አስተናጋጅ ሀገር ድምፅ ከመሰጠቱ አንድ ቀን በፊት ገንዘብ ትብቀብሎዋ ሲል ማስነበቡን ተካትሎ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ማኅበር የአሰራር ሕግ በመጣስ በሚል ለጊዜዉ የአባልነት

ምስል Getty Images/AFP/M. Thompson

ሮጀር ፊዲሪር  እና ጋብሪ ሙግሩዛ የ2017 የዊምብልደን ሻንፒዮን ሆኑ። በታላቅዋ በብሪታንያ ሲልቭርስቶን የተካሂደው የፎርሙላ ዋን የግራንፕሪክስ ውድድር በሉዊስ ሀምልተን  አሽናፊነት ተጠናቀቀ።

ፊፋ የ 2022 የዓለም ዋንጫ አዠጋጅ ኳዋታር የዝግጅት ፍቃድዋ ነጠቀ ሲባል የተሰራጨውን ዜና ውሸት ሲል አስተባብሏል።

በኬንያ መዲና ናይሮቢ በተካሄደዉ የዓለም ከ18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዩና ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያዎች አገኝታለች፡፡ ሰለሞን ባረጋ በ3000 ሺህ ሜትር ለሀገሩ ወርቅ ሲያመጣ ሂሩት መሸሻ በ800 ሜትር፣ አለሙ ቂጤሳ በ2000 ሜትር መሰናክል ነሐስ አስገኝተዋል፡፡

ሰለሞን የሦስት ሺህ ሜትር ውድድር ያሸነፈው የራሱን ምርጥ ሰዓት በማስመዘገብ ጭምር ነው፡፡ አትሌቱ ውድድሩን በሰባት ደቂቃ 47 ሰከንድ 16 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ የውድድሩን አዘጋጅ የኬንያን ሁለት አትሌቶች አስከትሎ ገብቷል፡፡ በዚሁ ውድድር ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሯጭ ሚልኪሳ መንገሻ አራተኛ ወጥቷል፡፡

ምስል picture alliance/AP Photo/P. Dejong

ቀደም ብሎ በ800 ሜትር የተወዳደረችው ሂሩት መሸሻ በሁለት ደቂቃ ከ06 ሰከንድ 32 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች፡፡ ኬንያዊቷ ጃክሊን ዋምቢዩ ይህን ውድድር ያሸነፈች ሲሆን የሀገሯ ልጅ ሊዲያ ጄሩቶ ላጋት የብር ሜዳሊያውን ወስዳለች፡፡ ኬንያውያን በሰፊ ርቀት ባሸነፉበት የ2000 ሜትር መሰናክል ውድድር ዓለሙ ቂጤሳ ሦስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ግርማ ድሪባ አራተኛ ወጥቷል፡፡       

ባለፈው ረቡዕ የተጀመረው እና ትናንት እሁድ በተጠናቀቀው በዚሁ ሻምፒዩና ኢትዮጵያ አራት ወርቅ፣ ሦስት ብር እና አምስት ነሐስ በማስመዝገብ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአምስተኛ ደረጃ ጨርሳለች፡፡ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ኩባ እና አዘጋጇኬንያ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ቦታ ተቆጣጥረዋል፡፡ የአትሌቲክስ ቡድኑ ዛሬ ኢትዮጵያ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ሃና ደምሴ

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW