1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. የስፖርት መሰናዶ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2010

በዕለተ-እሁዱ የለንደን ማራቶን የተሳተፉት እውቅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ጥሩነሽ ዲባባ ስታቋርጥ ቀነኒሳ በቀለ ስድስተኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል። በወንዶች ምድብ የ21 አመቱ ቶራ ሹራ በ32 ሰከንዶች ተቀድሞ ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅs የሴቶቹን ውድድር ታደለች በቀለ 3ተኛ ሆና ጨርሳለች።

UK äthiopische Athleten beim London-Marathon
ምስል DW/H. Demisse

ስፖርት ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም.

This browser does not support the audio element.

ዕሁድ ሚያዝያ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሔደው የለንደን ማራቶን ኬንያውያን በበላይነት አጠናቀዋል። በሴቶች ጎራ የ34 አመቷ ኬንያዊት ቪቪያን ቼሪዮት በ2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በማጠናቀቅ አዲስ የራሷን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ አሽንፋለች።  

ውድድሩ ሲጀመር  ከ15 አመት በፊት በ ፓውላ ራድክሊፍ በርቀቱ ያስመዘገበችው 2 ሰዓት ከ15 ድቂቃ ከ25 ሰከንድ ይሻሻላል የሚል እምነት ነበር ። ለዚህም ያግዝ ዘንድ የወንድ አሯሯጭ ተሳትፈውበታል። ባለፈው አመት  2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ01 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ርቀቱን ያጠናቀቀችው ሜሪ ኪታኔ እና 2 ሰዓት ከ17ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ውድድሩን የጨረሰችው ጥሩነሽ ዲባባ የተሻለ ሰዓት ያስመዘግባሉ ከተባሉት ጎራ ይገኙበት ነበር። 

ምስል DW/H. Demisse

እስከ 16 ኪሎ ሜትር ድርስ ውድድሩ እንደታቀደለት የሚሂድ ይመስል ነበር። በተለይ ሜሪ ኪታኔ ጥሩንሽን አምልጣ ለመውጣት ስትሮጥ ፍጥነቷ በግማሽ ደቂቃ ከፓውላ ራድክሊፍ ፈጥና ነበር።  ውድድሩን በቀዳሚነት እየመራች ይሻሻላል ከተባለው ሰአት መራቅ ጀመረች። 28ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ስትድርስ ጭርሱን መዘግየት ጀመረች ፥በውድድሩ ጥቁር እና ነጭ መስመር ያለው መለያ ለብሰው የነበሩት  አሯሯጮች የታሰበውን ያህል ውድድሩን ማፍጠን አልቻሉም። ሙቀቱ ያቀልጥ በነበረው የለንደን አየር ጥሩነሽ ውድድሩን ትማራው ከነበረው ሜሪ ኪታኔ ጋር የነበራትን 52 ሰከንድ ልዩነት በ8 ሰከንድ አጥብባው አፍታም ሳትቆይ  30ኛው ኪሎ ሜትር ላይ አቋርጣ ወጣች። ሶስተኛ የነበረችው ቪቪያን ቼሪዮት ከ33ኛው ኪሎ ሜትር ቀዳሚነቱን ተረክባ ገሰገሰች። በአስደንጋጭ ፍጥነት ውድድሩን ይመሩት የነበሩት አትሌቶች አቅማቸውን ጨርሰው ከውድድር ሲወጡ እና ወደ ኋላ ሲቀሩ በዝግታ የጀመሩት አሸናፊዋች ሆኑ ።
ውድድሩን ሁለተኛ ሆና የጨረሰችው ሊሊያ ፕትሪጅ ከታላቅዋ ብሪታንያ ስትሆን ኢትዮጵያዊቷ ታደለች በቀለ 3ተኛ ከመውጣቷም በላይ 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ 41 ሰከንድ በመግባት አዲስ የራሷን ስዓት አስመዝግባለች።

ምስል DW/H. Demisse

በወንዶች የ33 አመቱ ኪንያዊ ኢሉውድ ኪፕቼጌ  ለሶስተኛ ጊዜ አሸንፏል። ኪፕቾጊ 2 ሰዓት ከ 04 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ ኢትዮጵያዊው ቶላ ሹራ ባልተጠበቀ ሁኔታ  በ32 ሰከንድ ተቀድሞ ሁለተኛ ሆኗል። ያለፈው አመት የፍራንክ ፍርቱ አሸናፊ የ21 አመቱ ቶላ ሹራ ውድድሩ ለመጨረስ 2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ 49 ሰከንድ  የፈጀበት ሲሆን ይህ  4 ተኛ ማራቶኑ ነው። አብረቅራቂውን የመም ውድድር ትቶ መሉ ሙሉ ለሙሉ  ወደ ማራቶን የገባው ሞ ፋራሕ አዲስ የብሪታንያ ሰአት በማስመዝገብ 3ኛ ሆኗል። 

ሐና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW