ስፖርት፤ ኅዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም
ሰኞ፣ ኅዳር 3 2011በእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ በማንችስተር ደርቢ ማንችስተር ሲቲ ባለድል መሆኑን ተክትሎ፤ በ 12 ኛዉ ሳምንት የጨዋታ መረሐ -ግብር ያለመሸነፍ ክብሩን ማስጠበቁ፤ በጀርመን ቡንደስሊጋ ቦሪስያ ዶትርሙንድ መሪነታቸዉን ማስቀጠላቸዉ፤ በብሪታንያዊዉ የፎርሙላ አንድ የመኪና እሽቅድምድም ተወዳዳሪ ሉዊዝ ሃምልተን በሳምንቱ መጨረሻ ያስመዘገበዉን ድል ተከትሎ የሚወዳደርበት የማርቸዲስ ቡድን የሻምፕዮንነት ክብር እንዲጎናፀፍ ማስቻሉ፤ የሚሉትና ሌሎችም ስፖርታዊ ጉዳዮች የተካተቱበት ነዛሬዉ ሳምንታዊዉ የሰኞ ምሽት የስፖርት ዝግጅት ላይ የሚተነተኑ ይሆናሉ።
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነቱ በፍቃዱ መልቀቁ መሰማቱ የዕለቱ ሌላ ዓበይት ዜና ሆኖ ነዉ ያረፈደዉ። አትሌት ኃይሌ መልቀቂያ ደብዳቤውን ለጠቅላላ ጉባኤ አባላት ማዘጋጀቱን ዛሬ ቦሌ በሚገኘው የራሱ ቢሮ ለስፖርት ጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ ነዉ ይፋ ያደረገዉ። በደብዳቤው እንዳመለከተውም እስከ ቀጣዩ የምርጫ ወቅት ድረስ ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ተክታ እንድትሰራ መወከሉ ተዘግቦአል። በኛ በኩል ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ለአጭር ቃለ መልልስ በእጅ ስልኩ ላይ ያደረግነዉ ጥሪ አልተሳካም ። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴን አግኝተን ቃለምልልስ ለማድረግ የምናደርገዉ ጥረት ግን ይቀጥላል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ