ስፖርት እና መገናኛ ብዙሃን
ሐሙስ፣ ግንቦት 1 2011ማስታወቂያ
ክሱ በተለይ ያተኮረው የስፖርት ዘጋቢዎች ላይ ነው። የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማሕበር ምክትል ፕሬዝደንት ወቀሳው ችግሩ በሚታይባቸው ላይ መቅረብ ሲገባው በደፈናው ሁሉም ላይ ወቀሳው መቅረቡ ተገቢ አይደለም ይላሉ። የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው ምንም እንኳን ሁሉም መገናኛ ብዙሃን እና የስፖርት ዘገባ አቅራቢዎች በዚህ ድርጊት ይሳተፋሉ ባይባልም፤ ከስፖርታዊ ጨዋነት አኳያ ክፍተት ያለባቸው መኖራቸውን አመልክተዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ብለቦች ደጋፊዎች በብዛት ለሊጉ ውበት እና ድምቀት እየሆነ መምጣቱ ቢታይም በአንጻሩ ግን ደጋፊዎች በሜዳ ውስጥ የሚፈጥሯቸው የስፖርታዊ ጨዋነት የጎደላቸው ድርጊቶች ችግር እየተፈጠሩ መሆኑ እየታየ ነው። ከፓሪስ ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝር ዘገባ አላት።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ