1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት፣ ግንቦት 14 ፣ 2009 ዓ.ም

ሰኞ፣ ግንቦት 14 2009

በመጭው ነሀሴ ወር በለንደን በሚደረገው የአለም አትሊቲክስ ሻምፒዮን ውድድር የሚያሸንፉት አትሌቶች  የሚያጠልቁት ሜዳልያ ቅርፅ እና ይዘት ይፋ ሆነ። ሜዳልያው ከተለመደው የክብ ቅርፅ በተለየ የአትሊቲክስ መወዳደሪያ ሜዳን ቅርፅ የያዘ ሲሆን በውስጡ የሁሉንም የአትሌቲክስ ውድድር አይነቶቲችና የለንደንን ታዋ ቂህንፃ ምልክት ያካተተ ምስል ያያዘ ነው።

Symbolbild Leichtathletik Laufen
ምስል picture-alliance/dpa/B. Thissen

ስፖርት፣ ግንቦትt 14 ፣ 2009 ዓም

This browser does not support the audio element.

እግር ኳስ
የእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጭዋታ እንደተጠበቀው አጓጊ ነበር ። 10 ጭዋታ 37 ጎሎች አስተናግድዋል። ትላንት ትልቁ የኳስ ጦርነት  በመጭው የሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን  የተደረገው ትግል ነበር ። ለ19 ተከታታይ አመታት በሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተካፍይ የነበረው የሰሚን ለንደኑ አርሰናል በአንድ ነጥብ ተበልጦ ከመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ የመካተት ህልሙ አክትሞዋል።
በጀርመን ቡንዲስ ሊጋ ባየር ሙኒክ ለ 5ተኛ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን፣ ታዋቂ ተጫዋቾቹንም በክብር ሸኝቶዋል ። በማይፈለገው ደረጃ ውስጥ ላለመካተት የተደረጋው ትግል ሀምቡርግ ተሳክቶለት በቡንዲስ ሊጋው ሰንባች ቡድን ሆንዋል። 
በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ሀሪ ኬን በ 29 ጎል የ 2017 ኮከብ ጎል አግቢ ሲባል በ ጀርመን ቡንዲስ ሊጋ ደግሞ ፒየሪ ኤምሪክ ኦባምያንግ በ 31 ነጥብ የዚህ የጨዋታ ዘመን ከፍተኛውን ጎል ከመረብ በማሳረፍ የክብር ሽልማቱን አግኝተዋል።
የሜዳ ቴኒስ 
በሜዳ ቴኒስ ውድድር ሰርቢያዊው ኖቫክ ጃኮቪች ትላንት በ 20 አመቱ ጀርማናዊ ተጋጣሚው 2ለ0 መሸነፉን ተከትሎ የቀድሞው የአለም  የሚዳ ቲንስ ቁጥር አንድ አንድሪያ አጋሲን  አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን አስታወቀ ። ዝርዝሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። 

ሀና ደምሴ

አርያም ተክሌ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW