1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳምንታዊዉ ስፖርት፤

ሰኞ፣ መስከረም 16 2009

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር ጎልደን ሌብል ሲል  ከፈረጃቸው 13 የጎዳና ውድድሮች  መካክል አንዱ የሆንው 43ኛው የበርሊን ማራቶን ውድድር ትላንት  ተካሂዶ ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆነዋል። 

Wilson Kipsang   Kenenisa Bekele Evans Chebet Berlin Marathon Deutschland
ምስል picture-alliance/dpa/M.Schreiber

ስፖርት መስከረም 16፣ 2009 ዓም

This browser does not support the audio element.


ምስል REUTERS

የ ጀርመን ዋና ከተማ ያስተናገደው የበርሊን ማራቶን  ቀነኒሳ በቀለ ኪንያዊውን አትሌት ዊልሰን ኪፕሳንግ በመጭረሻዎቹ ኪሎ ሜትር ጥሎ በመውጣት  ሲያሸንፍ  የማራቶንን የዓለም ክብረወሰን ሊያሻሽል 6 ሰከንድ ብቻ ነበር የቀረው።  ቀነኒሳ የገባበት ሰአት የኤትዮጵያ  ፈጣን ሰአት ነው።  በ2013 የ ዓለም ክብረወሰንን የሰበረው ኪንያዊው ዊልሶን ኪፕሳንግ በ10 ሰከንድ ተቀድሞ ሁላተኛ ሆኖ ገብቷል። ሌላው ኪንያዊ ኤቫን ቻቤት 2 ሰአት ከ 5 ደቂቃ ከ31 ሰክአድ ሶስተኛ ሆንዋል። 

ኢትዮጵያውያን ሲቶች  በድል ባጥለቀለቁት 43 ኛው የበርሊን  የሴቶች ማራቶን ቀዳሚ በመሆን የመራችው አበሩ ከበደ የገባችበት  ሰኣት 2 ሰአት 20ደቂቃ  45ሰከንድ  ሲሆን ብርሃን ዲባባ 2 ሰኣት 23ደቂቃ 58 ስከንድ ሁለተኛ ሩቲ ኣጋ 2 ሰኣት 24 ደቂቃ 41 ሰከንድ ሶስትኛ ሆናለች ።

ምስል Picture-Alliance/dpa/A. Maltsev

በሪዮ ኦሎምፒክ ከተሳተፉ የብሪታንያ አትሌቶች መካካል 53 የሚያህሉ የህክምና መረጃቸው ተሰርቆ ይፋ ሊሆን እንደሚችል የብሪታንያ የጸረ አበረታች ንጥረ ነገር ቢሮ ስጋቱን ባለፍው ሳምንት ገልጾ ነበር። 53 የብሪታንያ አትሌቶች  የህክምና  ውጤት መሰረቁ  የተነገረው  ፋንሲ ብርስ የተሰኛ የመረጃ ጠላፊዎች ቡድን በድረ ገጹ ይፋ ባደረገውን መረጃ መሰረት በማድረግ  ነው ። የመረጃ ጠላፊዎቹ ቡድን በድረ ገጹ ይፋ ካደረጋቸው 6 በተጨማሪ አትሌቶች መካከል የሞይ ፋራህ ስም ይገኝበታል።

 እግር ኳስ

 6ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፤ ቅዳሜ ድል በራቃቸው ቀይ ሰይጣኖች እና በአምናው አዳኝ ቀበሮዎች መካከል በተደረገው ጨዋታ ተጀምሯል። የጀርመን ቡንደስ ሊጋ፤ ዓርብ ቦርሲያ ዶርቱመንድ ቡንደስ ሊጋውን ከመሪው ባየር ሙንሽን ጋር  በነጥብ የተስተካከለብት 48 ሰአት ነበር።  ፍራይ ቡርግን 3ለ1 በማሻነፍ ዶርት ሙንድ ካደረጋችው 5 ጨዋታዎች 4 ቱን አሸንፎዋል። ዶርት ሙንድ በመጭው ማክሰኞ ሪያል ማድሪድን በሻንፒዮንስ ሊግ ያስተናግዳል ።

 የሚዳ ቴኒስ፤ የ ጀርመኑ ታዳጊ ወጣት አሌክሳንደር ዚቭየሪ  የ ዩ ኤስ ኦፕን ሻንፒዮኑን ስታንስል ቫርቪንካን በ ሲንት ፒተርስ በርግ ኦፕን የአለም የሜዳ ቴኒስ ዙር ውድድር አሸነፈ።  በሌላ በኩል ሰሪና ዊሊያምስ በመጭው ሳምንት ከሚጀመረው የቻይና ዎሀን የሜዳ ቴንስ ውድድር  ውጭ መሆንዋ ታወቀ ። 

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW