ስፖርት
ሰኞ፣ ጥር 5 2006ዮንግ ዑን ወዳጅ መሆኑ የሚነገርለት ዴኒስ ሮድማን፣ በሰሜን ኮሪያው መሪ የልደት በዓል ፤ ከሌሎች ኮከብ ተጫዋቾች ጋር «የበጎ ፈቃድ ውድድር »ያሉትን ጨዋታ ማሳየታቸው ታውቋል።
ለምን ወደ ሰሜን ኮሪያ ሄደ? ለምን ስለ ለሰብአዊ መብት አልጠየቀም በማለት ለነቀፉት የአገሩ ሰዎች፤ የተሻለ ውጤት የሚገኘው ለዘብ ባለ አቀራረብ መሆኑን ሳይጠቁም አላለፈም። ቤይጂንግ አኤሮፕላን ጣቢያ እንደደረሰ የሰሜን ኮሪያ ህዝብን በዚያ የሚፈጸመው ያሳዝነኛል፤ እኔ በበኩሌ ጥሩ ነገር ብቻ ነው ለማድረግ የሞከርሁ፣ ግን «እኔ ፕሬዚዳንትም ፤ አምባሳደርም አይደለሁም -- እኔ ዴኒስ ሮድማን ነኝ » ነው ያለው ባጭሩ። ወደ ሳምንታዊው የአስፖርት ዘገባ እናምራ--
የጀርመን የአንደኛ ምድብ እግር ኳስ ክለቦች ፣ ከታኅሳስ 14 ቀን አንስቶ እስከ ጥር 15 ፣ በክረምት ዕረፍት ሳቢያ ውድድር ስለሌላቸው ፤ አንዳንዶቹ ወደ ሞቃት አገሮች በመጓዝ ልምምድ ሲያደርጉ መሰንበታቸው ታውቋል። በብሪታንያ ፤ እስፓኝ ፤ ኢጣልያና በመሳሰሉት ሃገራት ግን በዛሬው የእስፖርት ዝግጅት እንደምንገነዘበው ውድድሩ እንደቀጠለ ነው።
እግር ኳስ ፤ አትሌቲክስ ፣ እስፖርትና ግብረ ሶዶማዊነት ፣ እንዲሁም የሜዳ ቴኒስ ፣ በዛሬው የእስፖርት ክፍለ ጊዜ ትኩረት የሚደረግባቸው ናቸው ።ለጥንቅሩ ሃይማኖት ጥሩነህ---
ሃይማኖት ጥሩነህ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ