ስፖርት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2006ማስታወቂያ
ትናንት በተካሄደው 34 ተኛው የለንደን ማራቶን ኬንያውያን ድርብ ድል ተቀዳጅተዋል ። በወንዶች ማራቶን ውድድሩን በወንዶች ኬንያዊው ዊልሰን ኪፕሳንግ በሴቶች ደግሞ ኢድና ኪፕላጋት በአንደኛነት ጨርሰዋል ። ዊልሰን ኪፕሳንግ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ክብረ ወሰንም ነው የሰበረው ። ለሁለተኛ ጊዜ የለንደን ማራቶን ባለድል ኪፕሳንግ ውድድሩን የጨረሰው በ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ 24 ሴኮንድ ነው ። ያለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊ ፀጋዮ ከበደ በሶስተኛነት አየለ በሽር ደግሞ በአራተኛነት ጨርሰዋል ። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባም ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቃለች ። አትሌት ኃይለ ሥላሴ ደግሞ ውድድሩን አቋርጦ ወጥቷል ። ኬንያውያን ድል የተቀዳጁበት 34ኛው የለንደን ማራቶን ፣ እንዲሁም፣ የእንግሊዝ ፣ የጀርመን እና የስጳኝ የእግር ኳስ ክበቦች ጨዋታ የሳምንታዊው የስፖርት ዜግጅታችን ትኩረት ነው ።
ሃና ደምሴ
አርያም ተክሌ