1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2006

አሜሪካዊው መብ ክፍለ እዝጊ ዛሬ የተካሄደውን 118ኛዉ የቦስተን ማራቶን አሸነፈ ። ትውልደ ኤርትራዊው መብ የቦስተንን ማራቶን በማሸነፍ የመጀመሪያው አሜሪካዊ ነው ።

Boston Marathon Meb Keflezighi
ምስል AFP/Getty Images

መብ ውድድሩን የጨረሰው በ2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ነው ።በሴቶች ደግሞ ኬንያዊቷ ሪታ ጄፕቶ ለሁለተኛ ጊዜ የቦስተን ማራቶንን በአንደኛነት አጠናቃለች ። ኢትዮጵያዊቷ ብዙነሽ ደባ 2ተኛ ማሬ ዲባባ ደግሞ ሶስተኛ ወጥተዋል ። በወንዶች ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን የጨረሱት ኬንያውያን ናቸው ።

በዛሬው ውድድር 35,755 ሯጮች ተካፍለዋል ።ባለፈዉ ዓመት በማራቶን ዉድድሩ ማብቂያ ፍንዳታ ከደረሰ ወዲህ ቦስተን ላይ የሩጫ ዉድድር ሲደረግ የመጀመሪያ መሆኑ ነዉ። ባለፈዉ ዓመት በደረሰዉ ፍንዳታ ሶስት ሰዎች ህይወታቸዉን ሲያጡ 264 ደግሞ ተጎድተዋል። ቀጣዩ የስፖርት ዝግጅታችን እዚያው ቦስተን በተካሄደ ሌላ የአትሌቲክስ ውድድር በእግር ኳስ በመኪና ሽቅድምድም እንዲሁም በሜዳ ቴኒስ ላይ ያተኩራል ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW