1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊላንድ የሥልጣን ርክክብ አደረገች

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 3 2017

አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ዛሬ ሥልጣን የተረከቡት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለመቋጨት በቱርክ ሸማጋይነት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለሰላም በተጨባበጡ ማግስት ነው። በስምምነቱ ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ ዘላቂ የባሕር በር ተጠቃሚነት እንዲኖራት ሁለቱንም ወገኖች የሚጠቅም የንግድ ሥምምነት ለማድረግ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

Somaliland | Neu gewählter Präsident | Abdirahman Mohamed Abdullahi
ምስል Solomon Muche/DW

የሥልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ሶማሊላንድን ያስመሰገነ ነው

This browser does not support the audio element.

የሥልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ሶማሊላንድን ያስመሰገነ ነው

እንደ ሀገር ከየትኛውም ሀገርም ሆነ ዓለም አቀፍ ተቋም እውቅና የላትም። የምርጫ ሂደታቸው፣ ውጤቱን የሚቀበሉበት እና የሥልጣን ርክክብ የሚያደርጉበት ባሕል ግን በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት የተለመደ አይደለም። እዚህ ሶማሊላንድ ውስጥ ይህንን የተመለከተው ሁሉም ነገር የዳበረ እና የሰለጠነ ነው። ባለፈው ህዳር በተካሔደው ምርጫ 64 በመቶውን ድምፅ በማግኘት ያሸነፉት የተቃዋሚው ፓርቲ ዳዋኒ ተወካይ አብዲራሕማን ሞሐመድ አብዱላሒ ስድስተኛው  የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሆነው ዛሬ ሀሙስ ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ የታየው የስልጣን ርክክብ ፍፁም ሰላማዊ እና በሁለቱም ወገን ደስታ የተሞላበት መሆኑ ዩዚህ ማሳያ ነበር።

ሀርጌሳ ውስጥ በተደረገው የሥልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ የቀድሞ ርዕሠ-ብሔር ሙላቱ ተሾመ እና የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳት ሙስጠፋ ሙሀመድ ተገኝተዋል። በዚሁ ወቅት ያነጋገርናቸው  የሶማሊላንድ ሰው ደስታቸውን በአማርኛ ለማጋራት ወደዋል።

በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር አስተያየት

በዚህ የሥልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ ከሞቃዲሾ የመጡት በሶማሊያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሪቻርድ ራይሊ ለሶማሊላንድ  "በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ብዙ ወዳጅ አላችሁ" ሲሉ ተደምጠዋል። ባለፈው ምርጫ ዴሞክራሲ በተግባር ከታየባቸው ኹነቶች አንዱን መመልከታቸውንም በማወደስ ገልፀዋል።

አብዲራሕማን ሞሐመድ አብዱላሒ ስድስተኛው የሶማሊላንድ ፕሬዝደንትምስል Solomon Muche/DW

"የሶማሌላንድ ሕዝብ ለዚህ ቀጣና ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ እና ለዓለም የእውነተኛ ዲሞክራሲ ስርዓት ምሳሌ ሰጥቷል።
ጓደኛችሁ፣ አጋራችሁ በመሆናችን በእውነቱ ኩራት ይሰማናል። እኛ ለረጅም ጊዜ አብረናችሁ ነበርን። ዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች በርካታ አገሮች ጭምር።  ለወደፊትም ከጎናችሁ ነን"።

ከውጭ የመጡ የሶማሊላንድ ተወላጅ አስተያየት

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተካረረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት የሆነው  የኢትዮጵያ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ የባሕር በር የሚሰጥ እና በምትኩ እውቅና እንደሚያስገኝ ተገልፆ የነበረው የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን በሂደት ላይ መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። አልሸባብን በመዋጋት ለዓመታት የጋራ ግብ እና ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሆድና ጀርባ አድርጎ ከቃላት ያለፈ የዲፕሎማሲ ቁርቁስ ውስጥ ከቷቸው የቆየውም ይሄው ጉዳይ ነበር። ሌላኛው አስቱያየት ሰጪ ተከታዩን ብለዋል

"እጅግ ተደስቻለሁ። ምክንያቱም ምርጫው ፍትሐዊ ነበር። እናም ሰላማዊ። በሁሉም አቅጣጫ። በምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብ። ሁሉም ቦታ። ዛሬ ደግሞ ሁሉም ውጤቱን እያከበረ ነው። ሁላችንም ደስተኞች ነን"

ሀርጌሳ ውስጥ በተደረገው የሶማሊላንድ ሥልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ የቀድሞ ርዕሠ-ብሔር ሙላቱ ተሾመ እና የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳት ሙስጠፋ ሙሀመድም ተገኝተዋልምስል Solomon Muche/DW

የቱርክ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የማሸማገል ጥረት 

አዲሱ  የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ዛሬ ሥልጣን የተረከቡት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለመቋጨት እና ወደ ሰላም ለመምጣት በቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አሸማጋይነት የሁለቱን ሀገራት መሪዎች ትናንት ለሰላም ካጨባበጡ ማግስት ነው። በዚሁ የትናንቱ ግንኙነት ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ ዘላቂ የባሕር በር ተጠቃሚነት እንዲኖራት ሁለቱንም ወገኖች የሚጠቅም የንግድ ሥምምነት ለማድረግ እንደሚሰሩ መስማማታቸው ተገልጿል። 

ሰሎሞን ሙጬ 

ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW