ሶማሊያና የጋዜጠኞች ስቃይ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 22 2003ማስታወቂያ
በ2010 በ25 ሀገራት ከስራቸው ጋር በተያያዘ 57 ጋዜጠኞች መገደላቸውን ያመላከተው የአር.ኤስ. ኤፍ ሪፖርት ፓኪስታን በዓመቱ የጋዜጠኞች ግድያ የበረከተባት ሲል በመጀመሪያ ደረጃ አስቀምጧታል። ሶማሊያ ከ8ቱ ለጋዜጠኞች የከፉ ሀገራት አንዷ ሆና ተጠቅሳለች። መሰረቱን መቅዲሾ ያደረገው ሸበሌ ራዲዮ ሰራተኞቹን በግድያና በስደት እያጣ እንደሆነ ገልጿል። መሳይ መኮንን የሸበሌ ሬዲዮ አዘጋጅን በማነጋገር ያሰናዳው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።
መሳይ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ