1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊያ-የጋዜጠኞች መገደያ

ሰኞ፣ ሰኔ 1 2001

ዳይሬክተሩ-ሙክታር ወድቋል።ሁለተኛዉ ደሙን እያዘራ-ሮጠ።ገዳዮች ተከተሉት።ግን አላገኙትም።አራት ደቂቃ ያሕል እንዳሯራጡት መሰወሩን ሲያዉቁ።መሬት-ተዘርሮ ወደሚያጣጥረዉ ሙክታር ተመለሱ።እና---እንደገና ጀትልማን።

ሐብት ንብረታ ጠፍቷል-ጋዜጠኞቹም እጠፉ ነዉምስል dpa

እዚሕ-ቦን ጀርመን በተዘጋጀዉ የመገናኛ ብዙሐን አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የተካፈሉት ሁለት የሶማሊያ ጋዜጠኞች ሥለ ሥራ፥ኑሮ፤ ችግራቸዉ ለጉባኤተኞች ለማስረዳት ሲዘጋጁ መቃዲሾ አጠገብ አንድ ባልደረባቸዉ ታገተ።ነገ-ሳምንቱ ማክሰኞ።ሁለቱ ጋዜጠኞች ከሮብ-እስከ አርብ የሚሉትን ብለዉ ከቦን በተሰናበቱ ማግስት ደግሞ መቅዲሾ ዉስጥ ሌላ ባልደረባቸዉ ተገደለ።ሌላዉ ቆሰለ።እሁድ።ሌላ ቀን-ሌላ ሞት፥ሌላ ጥፋት።ሶማሊያ።-የእዉቅ ነዉጠኛ ፖለቲከኛዋ-መቁሰለም ተዘግቦባታል።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ። ከሶማሊያ ጥቅል-ግድያ፥ ስቃይ ምስቅልቅል መሐል የጋዜጠኞችዋን ነጥለን ለመቃኘት እንሞክራለን ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።

ነጋሽ መሐመድ/አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW