ሶማሌ ላንድ ነጻ አስተዳደር የመሰረተችበት 33ኛ ዓመት በለንደን ተከበረ
እሑድ፣ ግንቦት 11 2016የሶማሊላንድ ከ1991 እ፡ኤ፡አ ከዋናዉ ሶማሊያ ራሷን ገንጥላ ሉዓላዊ አስተዳደር ከመሰረተች እነሆ 33 አመታት ተቆጥረዋል
ይህንን በማስመልከት በለንደን የሚገኘው የሶማሊላንድ ከፍተኛ መልዕክተኛ ቢሮ የዚህን 33ኛ አመት በዓል በለንደን ኩይን ሜሪ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ብዙ እንግዶች በተገኙበት ትናንት ቅዳሜ ምሽት ተከብሯል። በዚሁ በዓል ላይ በርካታ ምሁራን ነጋዴዎች የፓርላማ አባላት እና የብሪታንያ መንግስት የታወር ሀምሌት ምክትል ከንቲባ እና የሶማሊላንድ ወዳጆች ህብረት አባላት ተገኝተዋል። ወ/ሮ ኤድና አደን ኢስማኤል የቀድሞዋ ሶማሊላንድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ሶማሌላንድ ዕውቅና የምታገኝበትን ሥምምነት ከኢትዮጵያ ጋር በሁለት ወራት ገደማ ትፈራረማለች ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ ሚኒስትር ተናገሩ
በተጨማሪ በምሽቱ ምሁራን ነጋዴዎች እና የብሪታንያ ዜግነት ያላቸዉ የሶማሊላንድ ወዳጆች ቡድን አባላት ተገኝተዋል። በብሪታንያ ከፍተኛ መልዕክተኛ የሆኑት አቶ አብዲ ሄርሲ በበኩላቸወእ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ጥሪውን አክብረው የተገኙትን እንግዶች አመስግነዉየሶማሊ ላንድ አገር መሆንዋን የሚያስረዳ እ፣ኤ:አበ1960 ከብሪታንያ የተሰጠ የውሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለችቅና ሰርተፊኬት ይፋ መሆኑ የዘንድሮውን በዓል ልዩ አድርጎታል ብለዋል።
ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች
“ክቡራን አእንግዶች እንኳን በዓላችንን አብረን ለማክበር እዚህ ተገኛችሁ። ለዚህም የተሰማኝን ደስታ ስገልፅ በከፍተኛ ስሜት ነው። ከሁሉ በማስቀደም በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙትን የተለያዩ ታዳሚዎች ለማመስገን እወዳለሁ፣ የዛሬውን በዓል ልዩ የሚያደርገው እኤአ በ1960 ከብሪታንያ የተሰጠን የበፃነት ሰርተፊኬት ይፋ የሚሆንበት ቀን በመሆኑ ነው።”
በተጨማሪም የታወር ሀምሌት ም/ከንቲባ አቶ ዐሊ አህመድ ሻህ አጠር ያለ ንግግር ሲያደርጉ
“ክቡራን የሶማሊ ላንድ ዜጎች እና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በዚህ የ33ኛ አመት በዓል ላይ ተገኝቸ ንግግር በማድረጌ የተሰማኘን ደስታ እገልፅላችኋለው ለ33 አመት የሉዓላዊነት አገርነት መንግስትነት ለማግኘት የሚያደርጉትን የሶማሊላንድ ትግል ሁልጊዜም እንደደገፍን ነዉ ታወር ሀምሌት ብዙ የሶማሊ ላንድ ዜጋዎች የሚኖሩበት ወረዳ ሲሆን በብዙ የልማት እና የጤና የትምህርት ተግባራት ላይ ብዙ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ዜጎች ናቸው ለዚህም ከዚህ ህዝብ ጋር መቆሜ ሁልጊዜም ያስደስተኛል።”
መኮንን ሚካኤል
ታምራት ዲንሳ