1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማልያ ከኢጋድ እወጣለሁ ስትል አስፈራራች

ሐሙስ፣ ጥር 20 2013

ሶማልያ እና ኬንያ በገጠሙት ዉዝግብ ሶማልያ ከምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት «ኢጋድ» እወጣለሁ ስትል አስፈራራች። ሶማልያ ትናንት ይህን የገለፀችዉ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለዉን ዉዝግብ እንዲያጣራ ኢጋድ የሾመዉ አጣሪ ቡድን የሶማልያን ጥያቄ ዉድቅ ካደረገ በኋላ ነዉ።

Kenia Nairobi | Präsident Somalia | Mohamed Abdullahi Mohamed
ምስል Yasuyoshi Chiba/AFP/Getty Images

የሶማልያና የኬንያ ዉዝግብ ወዴት ያመራ ይሆን?

This browser does not support the audio element.

 

ሶማልያ እና ኬንያ በገጠሙት ዉዝግብ ሶማልያ ከምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት «ኢጋድ» እወጣለሁ ስትል አስፈራራች። ሶማልያ ትናንት ይህን የገለፀችዉ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለዉን ዉዝግብ እንዲያጣራ ኢጋድ የሾመዉ  ቡድን የሶማልያን ጥያቄ ዉድቅ ካደረገ በኋላ ነዉ። ሶማልያ በበኩልዋ ድርጅቱ ግልፅ እና ነፃ ያልሆነ ወገንተኛ ስልትል የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት «ኢጋድ»ን ወርፋለች። ባለፈዉ ሳምንት የሶማሊያ መንግሥት ሉዓላዊነቱንና ዓለም አቀፍ ሕግና ስርዓትን መሠረት በማድረግ የሃገሪቱን አንድነትና ሉዓላዊነት የመጠበቅና ሃገሪቱን የማረጋጋት ሕገ መንግሥታዊ ግድታውን ለመወጣት ከኬንያ መንግሥት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን ለማቋረጥ ወስኗል ስትል ማስታወቅዋ አይዘነጋም። በሶማልያ እና ኬንያ መካከል እየከረረ የመጣዉ ዉዝግብ ለሃገራቱ ፤ ለአፍሪቃ ቀንድ ብሎም ፤ ለኢጋድ ምን አንደምታ ይኖረዉ ይሆን?  

አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW