1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግስት በሶማሊያ ያሉ ዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት

ዓርብ፣ የካቲት 15 2016

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዶክተር መለስ አለም ሁለት ሉዓላዊ ሃገሮች አንዱ ከሌላው ጋር ስምምነት ቢያደርጉ አግራሞት የሚፈጥር አደለም ብለዋል። በማሕበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚነዙ መረጃዎች ልክ አለመሆናቸውን በማከል።

አምባሳደር መለስ አለም የውጭ ዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
አምባሳደር መለስ አለም የውጭ ዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይምስል Solomon Muche/DW

መንግስት በሶማሊያ ያሉ ዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት

This browser does not support the audio element.

የቱርክና የሶማሊያ ስምምነት ለኢትዮጵያ ስጋት?

የሶማልያ የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት ከቱርክ ጋር የተደረገውን የመከላከያና የኢኮኖሚ ትብብር አጽድቋል። ስምምነቱን ተከትሎ የቱርክ የመከላከያ ሚኒስቴር ትላንት እንዳለው ቱርክ የሶማሊያን የውሃ ግዛት እንደምትጠብቅ አስታውቋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለጉዳዩ በተለይ ለDW በሰጠው መግለጫ ሁለት ሉዓላዊ ሃገሮች አንዱ ከሌላው ጋር ስምምነት ቢያደርጉ አግራሞት የሚፈጥር አይደለም ብሏል። 
የሶማልያ ምክርቤት ከቱርክ ጋር የተደረገውን የወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ የጋራ ስምምነት አጽድቋል። ይህን ተከትሎ የቱርክ የመከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሮይተርስ ትላንት እንደዘገበው  የሁለቱ ሃገራት ስምምነት በመካከላቸው ያለውን ትብብር ያጠናክራል ብሏል።

ከሶማልያ በቀረበላት ጥያቄ መሰረት ቱርክ የሶማልያ የውሃ ግዛት ከህገወጥ ተግባራት ለመጠበቅ ድጋፍ ታደርጋለችም ብሏል። ይህን ተንተርሶ በተለይ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ በርካታ ስጋት አዘል አስተያየቶች እየተንሸራሸሩ ነው። ይህ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ነው የሚሉ ትችቶችም እየተንሸራሸሩ ነው።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዶክተር መለስ አለም ሁለት ሉዓላዊ ሃገሮች አንዱ ከሌላው ጋር ስምምነት ቢያደርጉ አግራሞት የሚፈጥር አደለም ብለዋል። በማሕበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚነዙ መረጃዎች ልክ አለመሆናቸውን በማከል።
"ሁለቱ ሃገሮች ሉአላዊ ሃገሮች ናቸው። አንዱ ከሌላው ጋር ስምምነት ቢያደርጉ አግራሞትን የሚጭር አደለም። ከዛ ውጭ ግን ኢትዮጵያና ሱማልያ በጣም ጠንካራ ግኑኝነት አላቸው። ጊዚያዊ የሃሳብ ልዩነቶች የሚለያቸው አደሉም። በተመሳሳይ ኢትዮጵያና ቱርክ ዘመናት ያስቆጠረ ግኑኝነት አላቸው። በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጠንካራ ትስስር አለን። በርካታ የቱርክ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ። አብነት የሚሆን ሽርክና ነው ያለን። በመሪዎቻችን ደረጃም ጠንካራ ወዳጅነትና ቅርርብ አለን። በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጭ ሁሉ እውት ነው ብሎ መውሰድ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም።  "

መንግስት በሶማሊያ ያሉ ዜጎች ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት
ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በሶማሊያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ዛቻና ድብደባ እንደደረሰባቸው ለጣቢያችን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በሶማሊያ ያሉ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ምን እያደረገ ነው ስንል አምባሳደር ዶክተር መለስ አለምን ጠየቅናቸው።
"የዜጎቻችን መብታቸውና ክብራቸው የመጠበቅ የመንግስት ሃላፊነት ነው። ይህ ግን በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ የሚሰራ ስራ አደለም። ከየአገራቱ መንግስታት ጋር በሚኖር ትብብር የሚደረግ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የሶማሊላንድ ፕረዚደንት ሙሴ ባሂ አብዲ የመግባቢያ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላምስል TIKSA NEGERI/REUTERS

የኬንያ የቪዛ ክፍያ ስለመነሳት
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ኬንያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ወደ አገሯ የሚገቡ ዜጎች በበይነመረብ እንዲመዘገቡና የ34 ዶላር ክፍያ እንዲከፍሉ የጀመረችውን አሰራር ማንሳቷን አሳውቃለች። በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ የኬንያ መንግስት ጥያቄያችን በአፋጣኝ ተቀብሎ ምላሽ መስጠቱ አስደስቶኛል ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል። ኬንያ ይህን አሰራር የተከተለችው ባለፉት አመታት ከኢትዮጵያ ጋር በገባችው የዲፕሎማሲ መንገራገጭ ጋር ተያይዞ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ሲገልጹ ተደምጠዋል። ቃልአቀባዮ ዶክተር መለስ አለም ግን እንደዚህ አይነት አስተያየቶችከኬንያ ጋር ያለንን ጠንካራ ወዳጅነት ካለመገንዘብ የሚመነኝ ነው ብለዋል። ከኬንያ ጋር ያለው ግኑኝነት ከጊዜ ጋር የማይዋዥቅና ጥብቅ መሆኑን በማከል።
ኬንያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ወደ አገሯ የሚገቡ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ጥላው የነበረው የ34 ዶላር ክፍያ የተነሳ ቢሆንም በበይነመረብ የሚደረግ ቅጽ የመሙላት ግዴታ ግን አሁንም እንደቀጠለ ይታወቃል።


ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ኅሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW