ሶማልያ፡ የኢጋድ ምክክርና በሰሜን ሶማሊያ የተጣሉ ጥቃቶች
ረቡዕ፣ ጥቅምት 19 2001![ሶማሊላንድ](https://static.dw.com/image/3530277_800.webp)
ማስታወቂያ
በዚሁ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ በጠራው ጉባዔ ላይ የሶማልያ ጊዚያዊ ሁኔታ በዋነኝነት ተመክሮበታል። በዚሁ ጊዜ ዛሬ በሶማሊላንድ ርዕሰ ከተማ ሀርጌሳና በወደብ ከተማ ቦሳሶ በአንድ ጊዜ አካባቢ በተጣሉ አምስት የቦምብ ጥቃቶች በርካቶች መሞታቸውና ብዙዎች መቁሰላቸው ተሰምቶዋል። ለጥቃቱ እስካሁን ሀላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም።