1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶሪያ ከአሳድ አገዛዝ በኋላ

ሰኞ፣ ነሐሴ 7 2004

የሶርያ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ዲፕሎማት የአልአሰድን አስተዳደር መክዳታቸዉ ቀጥሏል። በተመ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የሶርያ ከፍተኛ ተወካይ የሀገሬን ህዝብ መርዳት አልቻልኩም በሚል መክዳታቸዉን ዛሬ ይፋ አድርገዋል።

Turkey's Foreign Minister Ahmet Davutoglu, top right, and U.S. Secretary of State Hillary Rodham Clinton meet with Syrian refugees in Istanbul, on Saturday, Aug. 11, 2012. (Foto:Jacquelyn Martin, Pool/AP/dapd)
Clinton in Istanbul Türkei Ahmet Davutogluምስል AP

ይህን ያስተዋለዉ ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ የሶሪያው ፕሬዚዳንት ባሻር አል- አሳድ አሁን ስልጣን ላይ ይሁኑ እንጂ በቅርቡ መዉረዳቸዉ አይቀርም በሚል ከእሳቸው በኋላ ስላለው ጊዜ ከወዲሁ ማሰብ ጀምሯል።

ሄለሪ ክሊንተን እና አቻቸዉ አህመት ዳቩቶግሉምስል AP

እንደ በርካታ ሀገሮች ሁሉ ዮናይትድ ስቴትስም የአሳድ አስተዳደር እስኪያበቃለት እየጠበቀች ነው። አሳድ ስልጣን መቼ እና እንዴት እንደሚለቁ ለጊዜው ማንም አያውቅም ነው ያሉት የዮናይትድ እስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄለሪ ክሊንተን። ቅዳሜ ዕለት የሶሪያ ቀውስን በተመለከተ ኢስታንቡል ቱርክ ላይ በተካሄደው ጉባኤ ከቱርኩ አቻቸዉ አህመት ዳቩቶግሉ ጋ በመሆን አንድ ቡድን ለማቋቋም ማሰባቸውን አሳውቀዋል። የሁለቱ አገሮች የስለላ ድርጅቶች እና ወታደሮች ከመቼውም የበለጠ በጋራ ተባብረው መስራት እንዳለባቸዉም ክሊንተን አሳስበዋል።

የዮናይትድ እስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄለሪ ክሊንተንምስል picture-alliance/dpa

«ቱርክ እነዚህን የጭካኔ ሰለባዎች ለመርዳት የምታደርገውን ተናግሬ አልጨርሰውም። መንግስት በቱርክ መጠልያ ለሚገኙት ሶሪያውያን ፣ መኖሪያ፣ ምግብ፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ወጪ አውጥቷል። አስፈላጊዉ ነገር በጨመረ ቁጥርም የእኛም ርዳታ አብሮ ማደግ ይኖርበታል። ዛሬ ተጨማሪ 5 ሚሊዮን ዶላር ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በመስጠት ለመተባበር ማቀዳችንን ለማሳወቅ እወዳለሁ። ተጨማሪ 500, 000 ዶላር ደግሞ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ሶርያዉያንን እንዲደግፍበት ቱርክ ዉስጥ ለሚገኘዉ ለዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ተቋም እንለግሳለን።»

የጀርመን ፓርላማ የውጭ ፖለቲካ ተመልካች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሩፕሬሽት ፖሌንዝምስል picture-alliance/ dpa

ዳቩቶግሉ በበኩላቸው ከጦርነት ለሚሸሹትን ከለላ ለመስጠትአንድ ከግጭት ነፃ የሆነ ቀጠና ሶሪያ ውስጥ መቋቋም እንደሚኖርበት ነዉ ያመለከቱት። ዮናይትድ እስቴትስ እና ቱርክ ብቻ አይደሉም ስለ ሶሪያ ወቅታዊ ሁኔታ የሚወያዩት ። የጀርመን መንግስትም ከነሀሴ መጀመሪያ አንስቶ አዲስ የአሰራር ዘዴ በርሊን ላይ ጀምሯል። ሀገራቸዉ ነፃ የሆነች ሶርያን ለማየት እንደምትሻ፤ የጀርመን ፓርላማ የውጭ ፖለቲካ ተመልካች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሩፕሬሽት ፖሌንዝ ተናግረዋል።

« የጀርመን መንግስት ለተለያዩ የሶሪያ ጎሳዎች ነፃነት ይቆማል። በዚኛው መንገድ ለመጓዝ ለተዘጋጁ እና የጀርመንን ድጋፍ ለሚጠይቁ በሙሉ ጀርመን ድጋፍ ትሰጣለች። »

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ በበኩላቸው አሳድ ደን ሀግ በሚገኘው ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ይሁንና ቬስተቬለ ለጀርመን ቢልድ ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በሶሪያ የደም መፋሰሱ እንዳይቀጥል፤ አሳድ በፍቃደኝነት አገር ለቀው ቢወጡ የክሱ ጉዳይ ለእሳቸዉ ቀዳሚ ጉዳይ አይሆንም ነዉ ያሉት። አልአሳድ ስልጣን እስካሁን የመልቀቅ ፍንጭ ባያሳዩም ተሿሚዎቻቸዉ መክዳት መቀጠላቸዉ ነዉ የሚታየዉ። ባለፈዉ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትራቸዉ ጥለዋቸዉ ሄዱ፤ ዛሬ ደግሞ ጄኔቫ ላይ በተመ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሶርያ ከፍተኛ ልዑክ ዳኒ አልባጂ ለህዝቤ ካልጠቀምኩ በሚል በዓለም መድረክ ከዷቸዉ።

ቬርነር ሽሚትስ

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW