ቃለ መጠይቅ ከአምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ጋር
ቅዳሜ፣ ግንቦት 16 2017
ማስታወቂያ
ሶስተኛው የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ ዕሮብ ዕለት ብራስልስ ተካሂዶ ውሳኔውን በማሳለፍና የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። ስብሰባውን የመሩት የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ወይዘሮ ካያ ካላስና የአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ካውንስል ሰብሳቢ ሚስተር ቴቴ አንቶኒዮ ሲሆኑ፤ በስብሰባውም 50 ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከሰባ በላይ ልኡካን የተሳተፉ መሆኑ ታውቋል ።
በቤኑሉክስ እና በአውሮፓ ሕብረት ተቋማት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ኢትዮጵያን ወክለው ከተሳተፉ ልዑኦች መካከል አንዱ ናቸው። ስለ ስብሰባው እና ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ስላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ አግኝቶ በአጭሩ አነጋግሯቸዋል።