1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሺ ቺንፒን አዲሱ የቻያና ኮምኒስት ፓርቲ መሪ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2005

ምዕራቡ አለም በቻይና ንግድና የሰብአዊ መበት አያያዝ ላይ ለሚሰነዝረው ትችት እንግዳ አይደሉም ። ሺ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ይበልጥ የሚታወቁት ሜክሲኮን በጎበኙበት ወቅት ፣ ቻይናን ከመውቀስ በቀር ሌላ ሥራ የሌላቸው ሲሉ ምዕራባውያንን በተቹበት አባባላቸው ነው ።

FILE - Chinese Vice-President Xi Jinping speaks to Egypt's President Morsi (not pictured) during their meeting in the Great Hall of the People in Beijing, China, 29 August 2012. The man expected to lead 83 million members of the Chinese Communist Party and rule 1.3 billion people for the next decade had not been seen in public for more than 10 days by Tuesday, September 11, 2012. EPA/HOW HWEE YOUNG/ POOL +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

ባለፉት 5 አመታት የቻያና ኮምኒስት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉት ሺ ቺንፒን ተሰናባቹን ሁ ጂንታውን በመተካት የፕሬዝዳንትነቱን ሥልጣን ተረክበዋል ።

ምንም እንኳን አዲሱ የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ሺ ለ 5 አመታት በምክትልነት ቢሰሩም የፖለቲካ አቅጣጫቸው ግን አሁንም ግልፅ እንዳልሆነ ነው የሚነገረው ። ለመሆኑ ሺ ቺንፒን ማናቸው ቀጣዩ የማቲያስ ቦሊንገር ዘገባ በማንንነታቸው ላይ ያተኩራል ።

ምስል AP

በቻይናው ፕሬዝዳንት በሁ ጂንታው ሥር አዲሱ ትውልድ የዛሬ 10 አመት ሥልጣን ሲይዝ የ ሁ ማንነት የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጥያቄ ነበር ። ፓርቲያቸው ይፋ ካደረገው ግለ ህይወታቸው ውጭ የሁ ማንነት ያኔም ሆነ ከ10 አመት በኋላ አሁን እምብዛም አይታወቅም  ። ዛሬም እንደዛሬ 10 አመቱ ስለተተኪያቸው ስለ አዲሱ የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ሺ ቺንፒን ተመሳሳይ ጥያቄ እየቀረበ ነው ። አሁን ግን ጥያቄውን የሚያቀርቡ ቻይናውያን መልስ ያገኛሉ ። የታዋቂዋ አቀንቃኝ ፔንግ ሊዩዋና ባለቤት ናቸው ። የሃገር ፍቅር በሚገለጣባቸው ዘፈኖቻቸው የሚታወቁት ፔንግ የሺ ሁለተኛ ባለቤት ናቸው ። ከትዳር ታሪካቸው ውጭ ሺ እምብዛም ጎልቶ የሚታወቅ ስብዕና የላቸውም ። ዊኪሊክስ

ምስል dapd

የተባለው ድረ ገፅ ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባገኘው መረጃ ሺ ን ምኞተ ብዙ ፣ የልሂቅ ቤተሰብና የተግባር ሰው መሆናቸውን ይገልፃል ። ሺ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ይበልጥ የሚታወቁት ግን ሜክሲኮን በጎበኙበት ወቅት ፣ ቻይናን ከመውቀስ በቀር ሌላ ሥራ የሌላቸው ሲሉ ምዕራባውያንን በተቹበት በዚህ አባባላቸው ነው  ።

«የተሳለቹና ምንም የማይሰሩ የውጭ ዜጎች ጣታቸውን ቻይና ላይ ከመጠቆም በስተቀር ሌላ ሥራ የላቸውም ። አንደኛ እኛ አብዮት ወደ ውጭ አንልክም ፣ ሁለተኛ ረሃምብ ሆነ ድህነትን ወደ ውጭ አንልክም ፣ በሶሶተኛ ደረጃ በሌሎች ጉዳዮች ጣልቃ አንገባም ። እና ምንድነው የምትፈልጉት ? »  

በዚህ አነጋጋሪ ትችታቸው የሚታወቁት ሺ እጎአ በ 1953 አም ነው የተወለዱት ። አባታቸው አብዮታዊ ጀግና ነው የሚባሉት ። ያደጉት በኮምኒስት ልሂቃን ስብስብ ውስጥ ነው ። ዘር ማንዘራቸው ሁሉ የፓርቲው ባለሥልጣናት የሆኑት ሺ በታዛቢዎች ዘንድ የፓርቲው ልዑል ነው የሚባሉት ። አባታቸው እጎአ በ1960 ዎቹ በቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረ ችግር ለአመታት ወሂኒ ወርደው ነበር ። በሚሊዮኖች እንደ ሚቆጠሩ ወጣት ቻይናውያን በቻይናው የባህል አብዮት ወደ ገጠሪቱ ቻይና ተልከው ነበር ። በሻንሺ ክፍለ ሃገር ውስጥ በሚገኝ የገጠር መንደር አመታት አሳልፈዋል ።

ምስል AP

ቤይጂንግ እንደተመለሱም ወደ ፖለቲካው አለም ዘልቀው ገቡ ። የኮምኒስት ፓርቲ አባል ሆኑ ። ያኔ አባታቸው ታስረው ነበር ። በቻይና ጦር ኃይል ሥራ የጀመሩት ሺ የመከላከያ ሚኒስትሩ ጌንግ ብያዮ ረዳት እስከመሆኑ ደረሱ ። ከዚያም የፓርቲው ፀሃፊ ሆኑ ። ለባህርዳርቻዎቹ የዝሄቺያንግ ና የፉጅያን ክፍላተ ሃገር አገረ ገዥነትም ተመረጡ ። መንግሥት ግዙፍ ሥራዎች በሚያከናውንበት በቻይና በነዚህ ጊዜያትም የግሉን ዘርፍ ፍላጎት በማዳመጥ ዝና አትርፈዋል ። በ2007 የፖሊት ቢሮ አባል በመሆን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኑ ። ሺ በምእራባውያን ግልፅ ተደርገው ነው የሚወሰዱት ። ሴት ልጃቸው ሃርቫርቫርድ አሜሪካን ስሟ ተቀይሮ ትምህርቷን እየተከታተለች ነው ። በወጣትነታቸው አሜሪካንን ተዘዋውረው አይተዋል ። ምዕራቡ አለም በቻይና ንግድና የሰብአዊ መበት አያያዝ ላይ ለሚሰነዝረው ትችት እንግዳ አይደሉም ። በቅርቡ አሜሪካንን በጎበኙበት ወቅት ቻይና በሰብአዊ መብት አያያዝ ረገድ ብዙ ፈተናዎች እንዳሉባት የተናገሩት ብዙዎችን አስገርሟል ።

« ቻይና ብዙ ህዝብ አላት ። የየክፍለ ሃገሩ እድገት በእጅጉ የተለያየ ነው ። በዚህ ሁኔታ  የሰብአዊ መብት ይዞታን ለማሻሻል ብዙ ፈተናዎች አሉ ። »

ማቲያስ ቦሊንገር

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW