1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሽታይንማየር፤ «በቻይና ያለዉ ሁኔታ አሳስቦኛል»

ሰኞ፣ ኅዳር 19 2015

እርምጃዎቹ በጣም ጥብቅ ለሆኑበትና አሁንም ተፈፃሚ ለሆነበት በቻይና ለሚኖረዉ ህዝብ ሸክሙ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አያዳግትም ። ለዚህም ሰዎች ትዕግስት በማጣታቸ እና ቅሬታቸውን በየጎዳናው እየገለፁ መሆኑን ተረድቻለሁ። እንደ አንድ ዴሞክራሲን እንደሚያራምድ ሰዉ፣ ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት የሕዝብ ጥቅም ነው ማለት እችላለሁ።

Bundespräsident Frank-Walter Steinmeier | Interview mit der Deutschen Welle 2022
ምስል Liesa Johannssen/Bundesregierung

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የቻይና ህዝብ የተጣለበትን የኮሮና ጥብቅ ህግጋትን በመቃወም አደባባይ እያሳየዉ ያለዉን ከፍተኛ ተቃዉሞ በተመለከተ ከ DW ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ምላሽ ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት «ከቤጂንግ እና ከበርካታ የቻይና ከተሞች የሚደርሱን ምስሎችን ስመለከት በጣም አሳዝኖኛል»።  በጀርመንም ቢሆን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የተደረገዉ ከፍተኛ ርብርብ እና ትግል የህዝቡን የየለት ህይወት በከፍተኛ ሁኔታ ነክቶት እንደነበር የሚታወቅ ነዉ።

«እርምጃዎቹ በጣም ጥብቅ ለሆኑበትና አሁንም ተፈፃሚ ለሆነበት በቻይና ለሚኖረዉ ህዝብ ሸክሙ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አያዳግትም ። ለዚህም ሰዎች ትዕግስት በማጣታቸ እና ቅሬታቸውን በየጎዳናው እየገለፁ መሆኑን ተረድቻለሁ። እንደ አንድ ዴሞክራሲን እንደሚያራምድ ሰዉ፣ ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት የሕዝብ ጥቅም ነው ማለት እችላለሁ።  እናም በቻይና ያሉ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ሃሳብን የመግለጽ ነፃነትን፣ የመቃወም ነፃነትን ያከብራሉ የሚለውን ተስፋ ይዘናል። እርግጥ ነው፣ማሳያዎቹ ሰላማዊ ሆነው እንደሚቀጥሉ ተስፋ አደርጋለለሁ»ሲሉ የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።»

በቻይና ባለፉት አሥርተ ዓመታት ውስጥ ያልታየ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ተቀስቅሶ በርካታ ሰዎች መታሰራቸዉን ተከትሎ ነዉ። ህዝባዊ ተቃዉሞዉ ሃገሪቱ የያዘችዉ ኮሮናን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት ፖለቲካ፤ ህዝቡ በየጊዜዉ ለምርመራ በመጠራቱ፤ የዝዉዉር እግድን ጨምሮ  የኮሮና መከላከያ ጥብቅ ህጎች ተግባራዊ ማድረግን ብሎም ተገልሎ መቀመጥ ህግ ሰለቸን በማለቱ ነዉ።  በሳምንቱ መጨረሻ በቻይና በርካታ ከተሞች የተቀሰቀሰዉ ከፍተኛ ተቃዉሞ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ መቀጠሉ ተነግሯል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች በዋና ከተማዋ ቤጂንግ በተለይ ዲፕሎማቶች በሚገኙበት አካባቢ ማታ ማታ የሚወጡ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መዉሰዳቸዉ ተሰምቷል ።

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW