ሽፈራዉ /ሃለኮ/ ተክል24 የካቲት 2001ማክሰኞ፣ የካቲት 24 2001በሳይንሳዊ ስሙ ሞሪንጋ ስቴኖፔታል፤ በአገርኛዉ ደግሞ በአንዳንድ አካባቢ ሽፈራዉ፤ በሌላዉ ስፍራ ሃለኮ፤ በሌሎች ስፍራዎችም ሌሎች ስያሜዎች አሉት። ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጥ የድሃ ወገን የሆነ ተክል ነዉ ይሉታል ያጠኑት ባለሙያዎች።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግ....እዚህም መትከል ይቻላል...ምስል dpa - Fotoreportማስታወቂያ ቅጠሉና ፍሬዉ ለምግብነት ከመዋሉ ባሻገር፤ ቅርፊትና ስራስሩ ሳይቀር ለመድሃኒትነት ይበጃል። ለመብቀል እጅግም ዉሃ አይፈልግም። በደረቅና ርጥበት በሌለበት የአየር ጠባይ አሳምሮ ይበቅላል። ይህ ተክል የሚሰጠዉ ጥቅም ከፍተኛ ሆኖ ሳላ በአገራችን ኅብረተሰቡ በቅጡ ምንነቱን ስላላወቀለት ትኩረት አላገኘም።