1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ቀውስ ውስጥ ገብቷል» የተባለው የምጣኔ ሃብት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 9 2014

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምጣኔ ሃብት በማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት፣ በኮሮና ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት «ቀውስ ውስጥ» ገብቷል እየተባለ ነው። መንግሥት ከፖሊሲ ያለፈ የመፍትሔ አማራጮችን ሊተገብር እንደሚገባ ዶቼ ቬለ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ ጠይቀዋል።

Äthiopien Währung Birr
ምስል Eshete Bekele/DW

«መንግሥት ከፖሊሲ ያለፈ የመፍትሔ አማራጮችን ሊተገብር ይገባል»

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምጣኔ ሃብት በማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት፣ በኮሮና ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት «ቀውስ ውስጥ» ገብቷል እየተባለ ነው። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ከዚህ ችግር እንዲወጣ «ሁለንተናዊ የመፍትሔ ማዕቀፍ» እንደሚያስፈልግ መክረዋል። መንግሥት በዚህ ዓመት የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት እና የውጭ ንግድን ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጌ እሠራለሁ ሲል ቃል ገብቷል። ሆኖም የሰሜኑ ጦርነት የተጨመረበት የዋጋ ንረት፣ የዕዳ ጫና ፣ የብድር ክልከላ ፣ የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ነዋይ ፍሰት መቀነስ ፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ስጋት እንዲሁም የዲፕሎማሲ ጫና መንግሥት በዓመቱ ያቀደውን ለማሳካት ፈተና እንደሚሆንበት ነው ባለሙያዎች የሚያሳስቡት። ይህም በመሆኑ መንግሥት ከፖሊሲ ያለፈ የመፍትሔ አማራጮችን ሊተገብር እንደሚገባ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ ጠይቀዋል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW