ቃለ መጠይቅ፣ የጁቢቲ መሪ ስልትና አካባቢዉ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 4 2013ማስታወቂያ
የጁቢቲዉ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ ከ20 ዓመት በላይ የያዙትን ስልጣን ቢያንስ ለሚቀጥለዉ 5 ዓመት እንደያዙ እንዲቀጥሉ ባለፈዉ አርብ ተመርጠዋል።ፕሬዝደንት ጌሌ እስካሁን ስልጣን ላይ የቆዩት እንደ ስልጣኑ ሁሉ የአገዛዝ ስልቱንም ከአጎታቸዉ በመዉረሳቸዉ ነዉ የሚሉ ታዛቢዎች አሉ።የዚያኑ ያክል ጌሌ ሲሻቸዉ እንደ አጎታቸዉ፣ ሲመቻቸዉ ደግሞ የራሳቸዉን ስልት በመከተል የትንሺቱን ስልታዊ ሐገር ሐብትና ሥልጣን ለራሳቸዉ፣ ለዘመድና ወዳጆቻቸዉ አከፋፍለዋል የሚሉ አሉ።
ጌሌን ለተጨማሪ ዘመነ-ሥልጣን ሕጋዊ ዋስትና የሰጠዉ ምርጫ ባለፈዉ አርብ የተደረገዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በአፋርና በኢሳ-ሶማሌዎች መካከል በተደረገዉ ደም አፋሳሽ ዉጊያ የጅቡቲ ወታደሮች ተካፍለዋል የሚል ወቀሳ በሚሰነዘርበት መሐል ነዉ።ድምፅ ከመሰጠቱ ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ጌሌ በትዊተር ባሰራጩት መልዕክት «ኢትዮጵያ የአዋሽን ዉሐ እያቀበችብን ነዉ» በማለት መዉቀሳቸዉ ተሰምቷል።
ጅቡቲ ከኤርትራ ጋር የገጠመችዉ ዉዝግብም እስካሁን ዘላቂ መፍትሔ አላገኘም።አርብ የተደረገዉን ምርጫ አስታከን የጌሌን መርሕና ጅቡቲ ባካባቢዉ የሚኖራትን ሚና በማሕደረ ዜና ዝግጅታችን በሰፊዉ ቃኝተናል።ለዝግጅቱ ማጠናከሪያ ከፖለቲካ ተንታኝና ከደራሲ ዩሱፍ ያሲን ጋር ያደረግነዉን ሙሉ ቃለ መጠይቅ ደግሞ እዚሕ ማድመጥ ትችላላችሁ።
ነጋሽ መሐመድ