1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ ምልልስ በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እስክንድር ይርጋ ጋር፦ክፍል አንድ

ሐሙስ፣ ኅዳር 26 2017

አምባሳደር እስክንድር ይርጋ የጀርመን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮጳና የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ነበሩ። ከዚያ አሰeቀድሞ በለንደንና በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በኤኮኖሚና በዲፕሎማሲ ዘርፍ ሃላፊነት ሰርተዋል።

Deutschland Berlin 2024 | Ambassador Eskinder Yirga, Botschafter Äthiopiens mit Steinmeier
ምስል Ethiopian Embassy Berlin

ቃለ ምልልስ ከአምባሳደር እስክንድር ይርጋ በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጋር

This browser does not support the audio element.

በጀርመን አዲሱ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እስክንድር ይርጋ ፣ሥራቸውን ከጀመሩ አሁን ሁለተኛውን ወር ይዘዋል።በአምባሳደርነት የተሾሙት  ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር ሲሆን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ያቀረቡት ደግሞ በዚህ ዓመት በጥቅምት አጋማሽ ላይ ነው።የዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ ለማሳደግ ምክክር ተደረገ

አምባሳደር እስክንድር በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲፕሎማሲው ዘርፍ ከአታሼነት ተነስተው እስከ መጨረሻው የስራ ሃላፊነት ደርሰዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ21 ዓመታት በላይ በተለያዩ የሃላፊነት ዘርፎች ያገለገሉት አምባሳደር እስክንድር ከኢትዮጵያ ውጭ ከጎርጎሮሳዊው 2011 ዓም አንስቶ ለ4 ዓመታት በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በካውንስለርነት፣ ከጎርጎሮሳዊው 2019 ዓ.ም.  እስከ 2021 ዓ.ም. በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዚያም በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኤኮኖሚና በዲፕሎማሲ ዘርፍ በሃላፊነት ሰርተዋል። የጀርመን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮጳና የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል በምክትል ዳይሬክተር ጀነራልነት አገልግለዋል።ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ በጀርመን ፍራንክፈር ከኢትዮጵያውያን ጋር ሊወያዩ ነው  

 

አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ምስል Ethiopian Embassy Berlin

ዶቼቬለ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በአዲሱ ሃላፊነታቸው ምን ሊያሳኩ እንዳሰቡ፣ጀርመናውያን ኢንቬስተሮችንና ቱሪስቶችን ለመሳብ በሚደረገው ጥረት እንቅፋት ሆኗል ስለሚባለው የሰላም እጦትና ተጨማሪ ተግዳሮች እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይም አነጋግሯቸዋል። ሁለተኛው ክፍል ሳምንት ማክሰኞ ይቀርባል።

የመጀመሪያውን ክፍል ቃለ ምልልስ ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን ማገናኛውን ይጫኑ።

 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ 



 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW