1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ቃ/መጠይቅ ከብርጋዲየር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ጋር

ዓርብ፣ ጥቅምት 30 2011

ብርጋዲየር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ሞት ተፈርዶባቸው የነበሩ፣ በኋላ ወደ እድሜልክ እስራት የተቀየረላቸው፣ ከዚያም በቅርቡ ከእስር የተለቀቁ ናቸው፡፡ ቀደም ሲልም የአማራ ዴሚክራሲዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነውም ተመርጠዋል፡፡

Äthiopien Brigadegeneral Asamnew Tsige
ምስል፦ DW/A. Mekonnen

ወደ ውትድርናው ዓለም ከመቀላቀላቸው በፊት በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ከዚም የአማራ ስራ አመራር በኃላፊነት ሰርተዋል፡፡ በኢትዮ- ኤርትራ  ጦርነት ወቅት የውትድርናውን ዓለም በመቀላቀል በኃላፊነት ሰርተዋል፤ እስከ ብርጋዴር ጀነራልነት ደርሰዋል፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ የተቋቋመው የአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በክልሉ ምክር ቤት ተሾመዋል፡፡  አሁን ደግሞ አዲስ የተቋቋመው የአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በቅርቡ በአማራ ክልል ምክር ቤት ተሸመዋል፡፡ የባሕር ዳሩ ዘጋቢያችን አለምነው መኮንን ስለቀደመው ሥራቸውና በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ምን እንዳቀዱና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ-መጠይቅ አድርጎላቸዋል፤ የድምፅ ማድመቻ ማዕቀፉን በጫን ሙሉ ቃለምልልሱን ይከታተሉ። 

አለምነው መኮንን

ተስፋለም ወልደየስ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW