ቅኝ ግዛትን መታገል የአፍሪካውያን የተቃውሞ ታሪክ ነው
ሰኞ፣ መጋቢት 9 2016
ቅኝ ግዛትን መታገል የአፍሪካውያን የተቃውሞ ታሪክ ነው። በምስራቅ አፍሪካ እና በታላላቅ ሀይቆች አካባቢ የጀርመን ቅኝ አገዛዝ የጀመረው የጸረ-ባርነት ትግል እያደገ በመጣበት ወቅት ቢሆንም በ1907 ግን አብዛኛው ምስራቅ አፍሪካ አካባቢዎች በጀርመን ቁጥጥር ስር ገብቶ ነበር። ይህ ሁኔታ ግን በበርካታ የምስራቅ አፍሪቃውያን እስካፍንጫቸው በታጠቁ የቅኝ ገዢ ኃይሎች ላይ ድፍረት የተሞላበት ተቃውሞ እንዲያስነሱ አድርጓል ።የጀርመን ቅኝ ገዢ ኃይል ወደ ናሚቢያ እግሩን ያስገባበት አጋጣሚ
በጎርጎርሳውያኑ 1885 በርሊን ውስጥ ተካሂዶ በነበረው ጉባኤ ጀርመን የዛሬዎቹ ታንዛኒያ ፣ ሩዋንዳ እና ብሩንዲ ፣ የሚገኙበትን የጀርመን ምስራቅ አፍሪካ ብላ በሰየመቻቸው ግዛቶች ላይ የይገባኛል ጥያቄ አነሳች ። ጥያቄው ግን በተጨባች ካለው እውነታው ይልቅ በንድፈ-ሀሳብ ላይ ተመስርቶ የቀረበ የቅኝ ግዛት የመሬት ጥያቄ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ጀርመን አካባቢው ላይ የመንግስትነት ስልጣን ስላልነበራት ነው። የጀርመን በምስራቅ አፍሪቃ መገኘት እውነታው ግን ሌላ ነው። ካርል ፒተርስን በመሳሰሉ የግል ቅኝ ገዢዎች የፈጸሟቸውን የመሬት ወረራ በመከተል ነበር።#የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ #Shadows of German colonialism
አዘጋጅ ካይ ኔቤ
ተርጓሚ እና ተራኪ ታምራት ዲንሳ