ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈዉ ዉሳኔ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2005ማስታወቂያ
17 ነጥቦችን በመጥቀስ በቀጣይ እንዲከናወኑ ዉሳኔ ማሳለፉን አመልክቷል። ጥቅምት 11 ቀን 2005ዓ,ም በሥርዓተ ፀሎት የተጀመረዉ የቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት ዓመታዊ ጉባኤ ካለፉት ዓመታት አንፃር ብዙም መረጃዎች ሳይሾልኩበት በዝግ የተካሄደ መሆኑ ነዉ የሚነገረዉ። እንዲያም ሆኖ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘዉና በአራተኛዉ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከሚመራዉ ሲኖዶስ ጋ ስለተጀመረዉ የእርቀ ሰላም ጉዳይ፤ እንዲሁም ስለፓርቲያርክ ምርጫና የምርጫ ስርዓት አበክሮ እንደሚነጋገር መሰማቱ አልቀረም። ትናንት ሲኖዶሱ ጉባኤዉን ማጠናቀቁን ይፋ በማድረግ የሰጠዉ መግለጫም የተጠቀሱት ነጥቦች እዉነትም እንደተባለዉ ከዋነኞች መነጋገሪ ጉዳዮች ተርታ መሆናቸዉን ጉባኤዉ ሲጠናቀቅ የወጣዉ መግለጫ አመልክቷል። መግለጫዉ በስደት በሚገኙና ሀገር ዉስጥ ባሉት የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች መካከል የተጀመረዉን እርቀሰላም አስመልክቶ በጥቅሉ እንዲቀጥል ሲኖዶሱ ወስኗል ከማለት ያለፈ ነገር አላመለከተምና ይህን እንዲያብራሩልን አቡነ ሕዝቅኤልን ጠይቀናቸዋል፤
ሸዋዬ ከገሠ
ሂሩት መለሰ