1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጣፊያ እና ቆሽት ጤና

ማክሰኞ፣ ኅዳር 10 2017

የውስጥ የሰውነት ክፍሎች ጣፊያና ቆሽት የአቀማመጥ ጉርብትናቸው አገልግሎታቸው ቢለያይም አንዱን በሌላው ለውጦ የመጥራት ነገር እንዳለ ልብ ብለዋል? የእነዚህ የሰውነት ክፍሎች ጤና ሊታወክ የሚችልበትስ አጋጣሚ? ካለእነሱስ መኖር ይቻል ይሆን?

የቆሽት እና የጣፊያ ጉርብትና
የቆሽት እና የጣፊያ ጉርብትና ፎቶ ከማኅደርምስል Zoonar/picture alliance

የጣፊያ እና ቆሽት ጤና

This browser does not support the audio element.

በንዴት ቆሽቴ ደበነ ሲባል እንሰማለን። ቆሽት በንዴት እንደተባለው ለጉዳት ይዳረግ ይሆን? «ሥጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ» ተብሎም ይተረታል። ይህን የውስጥ አካል ክፍል ጤና የሚያቃውሰው ምን ይሆን?

በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ አካል ክፍሎች በተፈጥሮ አቀማመጥም ሆነ በሕይወት የመኖራችን ሂደት እንዲቀጥል በማድረጉ በኩል አንዳቸው ከሌላቸው በአገልግሎት የመተባበራቸውን ያህል የአንዱ ጤና መታወክ የሌላኛውም ጉዳት የሚሆንበት አጋጣሚ ይኖራል። አንዳንዱ የሰውነት የውስጥ ክፍል በጤና እክል ተወግዶ አይደለም አገልግሎቱ ቢስተጓጎል በሕይወት መኖር ታሪክ ይሆናል። በአንፃሩ ይህ ቢወገድ ይሻላል ተብሎ የሚወሰንበት ተወግዶም ታማሚው በጤና ለመኖር የማይቸገርበት የውስጥ አካል ክፍል እንዳለ ሀኪሞች ያስረዳሉ። ከአድማጭ የተላከልንን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የጉበት፣ የሃሞት እና የቆሽት ቀዶ ህክምና ባለሙያ፤ በአዳማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ይታገሱ አበራ፤ ጣፊያ የምንለውን የአካል ክፍል ቆሽት ከሚባለው ጋር እያለዋወጡ የመረዳት ነገር ሊኖር እንደሚችል ነው ያስረዱን።

ጣፊያ

በተለይ በልጅነት በሽታ መከላከልን የሚያስችሉ የተፈጥሮ ቅመሞችን ከማመንጨት በተጨማሪ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎችን ያመርታል። ከዚህም በመነሳት ጣፊያ ለአንድ ሰው አካላዊ እድገት በሕጻንነት ጉልህ ሚና እንዳለው ዶክተር ይርጋለም አበራ አብራርተዋል። በትልቅነት ግን ጣፊያ የሚያመርታቸውን አስፈላጊ ቅመሞች መቅኒ ውስጥ መመረት ስለሚጀምሩ አገልግሎቱ ይቀንሳልም ባይ ናቸው። ውኃን አብዝቶ መጠጣት እና የኩላሊት ሥራ

ጣፊያ ብዙውን ጊዜ በአደጋ ምክንያት በሚከሰት ጉዳት ደም ፍሰት የማይቆምበት እክል ሲያስከትል በቀዶ ህክምና እንደሚወገድ፤ በዚህም ምክንያት ሰውየው ላይ የተጋነነ ጉዳት እንደማይደርስም ነው የተናገሩት።

ጣፊያው በቀዶ ህክውኃን አብዝቶ መጠጣት እና የኩላሊት ሥራምና የተወገደ አንድ ሰው ሊያደርገው ከሚገባው ጥንቃቄ ቀዳሚው ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ከሚያመጡ ተሐዋስያን እራሱን መከላከል እንደሆነ ነው ዶክተር ይታገሱ ያሳሰቡት።

የሰውነት የውስጥ ክፍል ምስል Ersin Arslan/Zoonar/picture alliance

  

ቆሽት

ከጣፊያ ጋር ተጎራብቶ የሚገኘው ይህ የሰውነት የውስጥ ክፍል በጣም አስፈላጊ ከሚባሉ የአካል ፍሎች አንዱ መሆኑን ነው የህክምና ባለሙያው ያስረዱት። ቆሽት ኢንሱሊን የተባለውን ንጥረነገር የሚያመርት የሰውነት ክፍል ሲሆን ኢንሱሊን የሰውነታችንን የስኳር መየኩላሊት የጤና ችግርጠን የሚቆጣጠር የተፈጥሮ ቅመም ነው። ቆሽት የምንበላው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በደንብ እንዲፈጭ ለዚህ የሚያስፈልጉ የተፈጥሮ ንጥረነገሮች የሚመረቱበትም የውስጥ አካል ክፍል ነው። የኩላሊት የጤና ችግር

ዶክተር ይታገሱ እንደሚሉት ቆሽት ሙሉ ለሙሉ በቀዶ ህክምና የሚወጣበት ጊዜ በጣም ውሱን ነው። ሊወጣ ግድ የሚሆነው በዋነኝነት በካንሰር ከተጠቃ እንደሆነም ነው አጽንኦት የሰጡት።

የጉበት፣ የሃሞት እና የቆሽት ቀዶ ህክምና ባለሙያ፤ በአዳማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር  ዶክተር ይታገሱ አበራ የሰጡትን ማብራሪያ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW