1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በሁለቱ የኢትዮጵያ ትልልቅ ክልሎች ለሚታየዉ ግጭት እልባት እንዲገኝለት መጠየቁ

ሥዩም ጌቱ
ሰኞ፣ መጋቢት 15 2017

በኢትዮጵያ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ዘላቂ እልባት እንዲያገኙ ሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ትልቁን ስፍራ እንዲሰጠው ተጠየቀ፡፡ ከሰሞኑ በሁለቱ ክልሎች መንግስት በታጣቂዎች ላይ ወሰድኩ ያለው ሰፋፊ ወታደራዊ እርምጃዎች በክልሎቹ ያለው የግጭት ይዞታ መባባሱን የሚሳይ ነው በሚል የሰጉ በርካቶች ናቸው፡፡

ፎቶ ማህደር ባህርዳር
በሺፊሮች ላይ የሚደርስ ጥቃት ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በሁለቱ የኢትዮጵያ ትልልቅ ክልሎች ለሚታየዉ ግጭት እልባት እንዲገኝለት መጠየቁ

This browser does not support the audio element.

በሁለቱ የኢትዮጵያ ትልልቅ ክልሎች ለሚታየዉ ግጭት እልባት እንዲገኝለት መጠየቁ 

በኢትዮጵያ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ዘላቂ እልባት እንዲያገኙ ሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ትልቁን ስፍራ እንዲሰጠው ተጠየቀ፡፡ ከሰሞኑ በሁለቱ ክልሎች መንግስት በታጣቂዎች ላይ ወሰድኩ ያለው ሰፋፊ ወታደራዊ እርምጃዎች በክልሎቹ ያለው የግጭት ይዞታ መባባሱን የሚሳይ ነው በሚል የሰጉ በርካቶች ናቸው፡፡

አንዴ ክፍ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝግ ብሎ የቀጠለው በሁለቱ ክልሎች በስፋት የተስተዋለው ግጭት እስካሁን በመሳሪያ ተሞክሮ ባለመሳካቱ ተፋላሚዎች ለጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሄ ትኩረት እንዲሰጡ ነው ፖለቲከኞች እና ተንታኞች የሚጠይቁት፡፡በኦሮሚያ እና ማዕከላዊ-ኢትዮጵያ ክልሎች አዋሳኝ ስጋት ያጫረው የታጣቂዎች እንቅስቃሴ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በለፈው ሳምንት አጋማሽ በይፋዊ ማህበራዊ ገጹ ላይ ኦሮሚያ ክልል “በምዕራብ ሸዋና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች አካባቢ የተሰማሩት የማዕከላዊ ዕዝ የሰራዊቱ አባላት “የሸኔ ቡድን” ባላቸው ታጣቂዎች ላይ ተወሰደ ባለው የጥምረት ወታደራዊ እርምጃ በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን በማሳቅ፤ “በርካታ” የቡድኑ አባላትን መግለደሉን 60 የሚሆኑትን ደግሞ ከጦር መሳሪያዎቹ ጋር በመማረክ ወታደራዊ እርምጃውን እንደሚያጠናክር ገልጿል።

መከላከያ ዓርብ አመሻሹን ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ደግሞ “ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛው ቡድን” ያሏቸው በአማራ ክልል በትጥቅ ውጊያ ላይ የሚገኙት የታጠቁ አማጺዎች “ዘመቻ አንድነት” በሚል ስያሜ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ በክልሉ በርካታ ዞኖች በመቶዎች መገደላቸውንና ብዙዎች ከጦር መሳሪያ ጋር መማረካቸውን አስረድቷል፡፡የአማራ ክልል ግጭት፣ የመኪኖች መቃጠልና የመንገድ መዘጋት

የግጭቶቹ መባባስ ጦስ

ፎቶ ማህደር ፤ ኦሮምያ ክልል ምስል፦ Fischer/Bildagentur-online/picture alliance

ላለፉት ጢቂት ለማይባል ጊዜያት በቀጠሉ በነዚህ ግጭቶች ለተሰላቹ ሰላማዊ ዜጎች የግጭቶቹን ማገረርሸት በበጎ ዜናነት አይመለከቱትም፡፡ አንጋፋው ፖለቲከኛ ሙላቱ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት እነዚህን የሁለቱን ክልሎች ግጭት መባባስ በአዎንታዊነት ካልተመለከቱት ናቸው፡፡ “ማንም ቢሸነፍ፣ ቢያሸንፍ ጦርነት ውጤት የለውም” ያሉት አቶ ሙላቱ፤ ችግሮችን የሚስከትለውን ጦርነት በማቆም ተኩስ አቁምም በማድረግ ወደ ምክክር ፊትን ማዞር ብቻ ዘላቂ እልባት እንደሚመጣ በአስተያየታቸው ገልጸዋል፡፡

አስተያየታቸውን የሰጡን ሌላው ባገረሸውና በቀጠለው ግጭት ስጋት እንደገባቸው የገለጹት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ፍልስፍና ረዳት ፖሮፈሰር ሲሳይ አሰምሬ ናቸው፡፡ “ይሄን በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት የጽንፈኞች ነው ብለው የማሳነስ ነገር አለ” የሚሉት ረዳት ፕሮፈሰር ሲሳይ፤ ወደ ግጭት ያስገቡ ስር የሰደዱ የህዝቡ ጥያቄዎች መኖራቸው ልብ ሊባል ይገባል ሲሉ አስተያየታውን ሰጥተውበታል፡፡በአማራ ክልል በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ ዝርፊያ መጨመር

ዘላቂ እልባቱስ ከየት ይምጣ

የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ በሚሰጣቸው አስተያየቶች በአገሪቱ በየትኛው አጽናፍ ላሉ ግጭቶች ሰላማዊ እልባት ለመስጠት ፍቃደንነቱን ስገልጽ ተደጋግሞ ተሰምተዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ግን የሰላም ስራዎቹ ግን ቁርጠንነትን የሚሹ ናቸው፡፡ ፖለቲከኛ ሙላቱ እንደሚሉት “የግጭቶቹ ምዕራፍ መቋጫው ፖለቲካውን በማዘመን ዲሞክራሲን መሰረታዊ አድርጎ በህዝብ ፍላጎት ላይ ቆሞ መስራት ነው” ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ በፊናቸው፤ “ትልቁ የመንግስት ስራ መሆን ያለበት ጦርን ከማስፈታትም በላይ የጦርነት አእምሮን የሚያስቀር ሰላማዊ የመተማመን የአእምሮ ስራ ነው” በማለት፤ የግጭቶቹ መራዘም “የውጪ ሃይሎችን ጋብዞ ኢትዮጵያን ያዳክማታል” የሚል ስጋታቸውን አጋርተዋል፡፡ስጋት ያጫረው የሰዎች ግድያ በኦሮሚያ ክልል

ፎቶ ማህደር ፤ ኦሮምያ ክልል ምስል፦ G. Fischer/blickwinkel/picture alliance

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የክልሎች ጸጥታ አካላት በኦሮሚያ ክልል ላለፉት ስድስት ዓመታት እንዲሁም በአማራ ክልል ለሁለት ዓመታት ግድም በደፈጣ የሚወጉት የየክልሎቹ አማጺያን ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ 

ፀሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW