1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

በሃማስ ጥቃት በርካታ ቤተ እስራኤላዉያን ተገድለዋል ተባለ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016

በተለያዩ ሃገራት «አሸባሪ ድርጅት» ተብሎ የተፈረጀዉ በፍልስጤሙ ሐማስ የተገደሉ እስራኤላዉያን ቁጥር ከ1,200 በላይ መድረሱ እየተዘገበ ነዉ። የእስራኤል ጦር ጋዛ ሰርጥን በቦምብና ሚሳዬል መደብደቡን ዛሬም ለ 6 ኛ ቀን ቀጥሏል። ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግ የሚጠይቀዉ ዓለም አቀፍ ሕግ እንዲከበር እያሳሰቡ ነዉ።

Terrorangriff der Hamas auf Israel | Auto und Kinderwagen bei Kibbutz Kfar Aza
ምስል RONEN ZVULUN/REUTERS

ፖሊስ፤ ወታደር፤ ፀጥታ አስከባሪ የነበሩ ቤተ-እስራኤላዉያን ተገድለዋል

This browser does not support the audio element.

 በዩናይትድ ስቴትስ፣ በአውሮጳ ኅብረት፣ በጀርመን እና በሌሎች ሃገራት «አሸባሪ ድርጅት»  ተብሎ የተፈረጀዉ በፍልስጤሙ ሐማስ የተገደሉ እስራኤላዉያን ቁጥር  ከ1,200 በላይ መድረሱ እየተዘገበ ነዉ። የእስራኤል ጦር ጋዛ ሰርጥን በቦምብና ሚሳዬል መደብደቡን ዛሬም ለ 6 ኛ ቀን እንደቀጠለ ነዉ። የተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ድርጅቶች ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግ የሚጠይቀዉ ዓለም አቀፍ ሕግ እንዲከበር እያሳሰቡ ነዉ።

 ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት

እስራኤል በአጸፌታው በጋዛ ሠርጥ በከፈተችው የመልሶ ማጥቃት የአየር ጥቃት ዘመቻ  ህጻናትን ጨምሮ ከ1350 በላይ ፍልስጤማዉያን መገደላቸዉም በሌላ በኩል እስራኤል ሃማስ ላደረሰዉ ጥቃት ምላሽ በጋዛ ሰርጥ እያደረሰች ካለዉ የአየር ድብደባ በተጨማሪ  ጋዛ ላይ  የኤሌትሪክ  የጋዝ እና የመጠጥ ዉኃ አቅርቦትም መቋረጡ ተዘግቧል።  

የእስራኤልና የሐማስ ጦርነት፤ የመንግስታት ዉዝግብ

በአሸባሪነት የተፈረጀዉ  የሃማስ ቡድን በእስራኤል ባደረሰዉ ከእስራኤላዉያንን ጨምሮ ከዩናይትድ ስቴትስ ፤ ከእንጊሊዝ ፤ ከፈረንሳይ የመጡ ዜጎች ተገድለዋል። ከመቶ በላይ ዜጎች በሃማስ ታፍነዉ ተወስደዋል።  ከሟቾች መካከከል በርካታ ቤተ እስራኤላዉያንም ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ ቤተ እስራኤላዉያን ተናግረዋል። 

አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW