በህወሀት ላይ የተሰነዘረው ወቀሳ25 የካቲት 2002ሐሙስ፣ የካቲት 25 2002በ1977 ዓም በኢትዮጵያ ደርሶ ለነበረው ከፍተኛ የረሀብ አደጋ መርጃ እንዲሆን ከዓለም አቀፍ በጎ አድራጊ ድርጅቶች የቀረበውን ርዳታ የዚያን ጊዜው ዓማጺ ሀይል -የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሀት ለፖለቲካ ስራና እና ለጦር መሳሪያ መግዣ እንዳዋለው ቢቢሲ የቀድሞ የህወሀት ባለስልጣናትን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ አስታወቀ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል APማስታወቂያ በትግራይና በወሎ በዚያን ጊዜ የተከሰተው የረሀብ አደጋ በብዙ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሰው ህይወትን ማጥፋቱ የሚታወስ ነው። ህወሀት ርዳታውን እንዴት ለራሱ አዋለው ስለተባለበት ጉዳይ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ በዚያን ጊዜ የህወሀት ከፍተኛ የአመራር አባል የነበሩትን ዶክተር አረጋዊ በርሄን በስልክ አነጋግሮ ያገኘው ማብራሪያ እነሆ። ገበያው ንጉሴ /አርያም ተክሌ ነጋሽ መሐመድ