በሊቢያ የጎርፍ አደጋ ዐሥር ሺህዎችን ቀጠፈ
ዓርብ፣ መስከረም 4 2016
ባለፈው እሁድ ሌሊትና ሰኞ በሊቢያ ምስራቃዊ ክፍል የደረሰው የጎርፍ አደጋና የውኃ መጥልቅለቅ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሊቢያውያንን ለሞትና መፈናቀል ዳርጓል። አንድ መቶ ሺ ኑዋሪዎች የነበሯት ዳርና የምትባለዋ የባህር ዳርቻ ከተማ አብዛኛው ክፍሏ በውኃ እንድሰመጠና አንድ ሦተኛው የሚሆነው ህዝቧም በውሀ እንደተወሰደ ወይም ያለበት እንዳልታውቀ እየተንገረ ነው። በከተማዋ ይህን የመሰለ አሳዛኝ አደጋ የተከሰተው በክተማው አቅራቢያ የነበሩ ሁለት ግድቦች ነፋስ የተቀላቀለበት ኃይለኛ ዝናብ ምክንያት ተደርምሰው ከተማውን በማጥለቅለቃቸው እንደሆነ ታውቋል። በዝናቡ ብዛት ግድቡን ጥሶ ከተማውን ያጥለቀለው ውኃ ኃይልና ፍጥነት የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም የቦንብ ፍንዳታ ያህል አስደንጋጭ እንደሆነና ሁኔታው የዓለም መጨረሻ ይመስል እንድነበር የሚሰሙ የሰቆቃ ድምጾች ያስተጋባሉ።
በውኃ የመጥለቅለቅና የጎርፍ አደጋዎች በበርካታዎቹ የዓለም ክፍሎችበአየር ለውጥ ምክንያት እየተከስተና አደጋም እያከስተሉ መሆኑ ቢታወቅም፤ የሊቢያው የክፋበት ምክንይት ግን አገሪቱ ካረቡ አብዮት በኋላ መንግስት አልባ ሁና ስለቆየችና ምንም አይነት ኃላፊነት የማይሰማቸው የየካባቢው የጦር አበጋዞች የሚያምሷት በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ምንም ይሁን ምን ግን የሚሰራ መንግስት ቢኖር ይህን አደጋ ማሰቀረት ባይቻል እንኳ በዚህ መጠን ጉዳት እንድይደርስ ማድረግ ይቻል እንደነበር ነው የአለም የሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሀፊ ፕሮፌሰር ፔቴሪ ታላስ የሚናገሩት፤ “ ትክክለኛ አሰራር ቢኖር፤ ሌላው ቢቀር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥና ሰዎችንም ከአካባቢው እንዲለቁ በማድረግ በርካቶችን ከሞት መታደግ ይቻል ነበር በማለት በቦታውም ይሁን ባገሩ ሀላፊነት የሚሰማው ወይም ስራውን የሚሰራ አካል አለመኖር ጉዳቱን እንዳከፋው ገልጸዋል።
ጎርፍ፣ ሌላዉ የአፍሪቃዉያን መጥፊያ
እ እ እ በ2011 አም በበርክታዎቹ ያረብ ገሮች የተከሰተው በተልምዶ የአረቡ የጸደይ አብዮት የሚባለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ፤ ያያኔዎቹን አምባ ገነኖች ክስልጣን እንዳወረደ ቢጠቀስም፤ አገሮቹ ግን ወይ እንደግብጽ ሌላ አምባገነን መሪ ተክተዋል፣ ወይ እንደ ሶሪያና የመን በርስ በርስ ጦርነት ደቀዋል፤ ወይ ደግሞ እንደ ሊቢያ በሁነኛ መንግስት አልባነት እስካሁን ዘልቀዋል። በዚያን ወቅት በአብዮት ይናጡ ከነበሩት የአረብ አገሮች፤ ምራባውያን በተለይ በሊቢያ በወታደር ሀይል ጭምርር ጣልቃ በመግባት ለበርካታ መታት ሊቢያን የመሩትን ኮሎኔል ጋዳፊ ከስልጣን መወገድ አፋጥነዋል። ኮሌኔል ጋዳፊ አምባገነን መሪ መሆናቸው ባይካድም የሊብያን ሀገረመንግስት በመገንባትና በማጻናት እንዲሁም ህዝቧ በሰፊው የዘይት ሀብቷ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ በኩል ግን ይጠቀስላሉ።
ሆኖም ግን ሊቢያ ከሳቸው በኋላና እክሳሁንም ድረስ ሁነኛና በህዝቡ የሚታመን መንግስት ሊኖራት አልቻለም። ጋዳፊን በማስወገድ አብረው ጣልቃ የገቡት ምራባውያን አንድ ማዕከላዊ የሊቢያ መንግስት ለመመስረት ግን አንድ እንድልሆኑ ነው የሚነገረው።
ተለያዩ የውጭ ሀይሎችን ከጀርባቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱት የሊቢያ ፖለቲከኞች በአንዳችም ነገር የማይስማሙ ለግልና ቡድን የፖለቲካ ፍላጎት ብቻ የሚታትሩ እንደሆነና የአሁኑ የጎርፍ አደጋ የተክስተውም በግዴለሽነትና ሀላፊነት ባለመወጣት ምክኒያት እንደሆነ ነው በሰፊው የሚነገረው ። አና ኤል ጎማቲ የተባሉ ሊቢያዊ መንግስታዊ ያልሆነው የስዲቅ እኒስቲቱት ዳይሬተር ይህንን ያረጋግጣሉ። “ በዴርና የትፈጠረው አደጋ በግዴለሽነት የተከሰተ ነው፡፤ ግድቡ ሞልት ሲፈስ ለበርክታ ሰአታት ሲታይ ነበር፡፤ ያኔ ግድቡን ማስተንፈስና ውህው ጉዳት ሳያደርስ እንዲፈስ ማድረግ ሲቻል፤ ለዚህ ግን ደንታ ያለው ሰው አልነበረም በማለት ይህም በሊቢያ አይነተኛው ችግር መሆኑን ገልጸዋል።
የዓለማቀፉ የግጭት ተከታታይ ድርጅት ክርይሥ ግሩፕ ተመራማሪ ወይዘሮ ክላውዲ ካዚኒም ከሁለቱ የሊቢያ መንግስታት አንዱም እንደዚህ ባለ የመሰረተ ልማት ግንብትም ሆነ እድሳት ለመስተፍና ለማቀድ ህጋዊነት ያለው አለመሆኑ የችግሩ አንዱ ምክኒያት ሁኗል ባይ ናቸው። እነዚህ ትሪፖሊና ቤንጋዚ ያሉ ሀይሎች በአሁኑ ወቅት ለተጎጂዎች እርዳታ እንዲደርስ በማድረግ በኩል እንኳ እየተባበሩ እንዳልሆነ የሚነገር ሲሆን፤ ከዚህ አይነት ብሄራዊ አደጋ ብኋላስ ተስፋ ይኖር ይሆን ወይ ተብለው የተጠየቁት ሊቢያዊ የፖለቲካ ተንትኝ ሚስተር ሳላህ ኤልባኩሽ፤ “ ተስፋ አደርጋለሁ ግን የሊቢያ የፖለቲክና ወታደራዊ ሀይሎች ከዚህ የሚማሩ አይመልሰኝም። በስልጣን ለመቆየት ወይም ስልጣን ለማግኘት ብቻ ነው የሚያልሙትና የሚሰሩት በማለት የሊቢያ መጻኢ ዕድል አሁንም ገና እደማይታወቅ አመላክተዋል ።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ታምራት ዲንሳ