በሕገወጥ ስደተኞች የተጨናነቀችዉ ጣልያን እና የአዉሮጳ ህብረት የመፍትሄ ሃሳብ
ማክሰኞ፣ መስከረም 8 2016
ጣሊያን ዛሬም እንደገና በስደተኖች እይተጥለቀለኩ ስትል ጩኸት እያሰማች ነው። ካለፈው የጥር ወር ወዲህ በሜዲትራኒያን ባህር በኩል ወደ ጣሊያን የገቡ ስደተኖች ቁጥር 126 ሺ ደርሷል። ይህ ማለት ባለፈው አመት በተመሣሳይ ወቅት ከነበረው በእጥፍ እንደሚበልጥ ነው የተነገረው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እራሷ ከዚህ ቁጥር በታች ኑዋሪዎች ባሏት በጣልያንዋ ላምፔዱዛ ደሴት በ24 ሰዓት ውስጥ ከሰባት ሺ በላይ ስደተኖች መግባታቸው የደሴቲቷን ኑዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒንም አስደንግጧል። የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ወይዘሮ ቮን ዴር ላይንም ከጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒ በደራሳቸው ጥሪ መሰረት ባለፈው እሁድ በቦታው ተገኝተው የተፈጠረውን ቀውስ ተመልክተዋል። ሁለቱ በጋራ በሰጡት መገልጫም፤ ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒ የስደተኖች ችግር መፍትሄ ማግኘት ያለበት አውሮፓ ውስጥ ሳይሆን እዚያው በአገራቸው ወይም በሚዘዋወሩባቸው አገሮች መሆን አለበት የሚለውን አቁማቸውን አጽኖት ስተውበታል። ችግሩ የጣሊያን ብቻ ስይሆን የአውሮፓ በመሆኑ በአስቸኳይ አውሮፓዊ መፍትሄ እንዲፈለግለት አሳስበዋል።በስደተኞች እና ፈላስያን ላይ ያተኮረው የአውሮጳ ህብረት ስብሰባ
ወይዘሮ ቮን ዴር ላይንም በትክክል ችግሩ የጣሊያን ብቻ እንዳልሆነ በማውሳት፤ ያለውን ችግርና ጫና ለመቀነስና በተለይም በላምፔዱዛ ያለውን ችግር ለመፍታት በህብረቱ በኩል የታቀደውን ባለአስር ነጥብ እቅድ ይፋ አድርገዋል። “አንደኛ የአዉሮፓ ህብረት ለጣሊያን የሚያደረገውን ድጋፍ ማሳደግና ማጠናከር፤ ሁለተኛ ከላምፔዱዛ ስደተኖችን ማስወጣትና ወደ ሌላ አባል አገሮች እንዲዛወሩ ማድረግ፤ የስደተኖች የስደተኘነት ጥያቄ በአስቸኳይ ውሳኔ እንዲያገኝ መስራትና ጥያቄያቸው ተቀባየነት ያላገኙትን በፍጥነት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ፤ የሚሉትንና ሌሎችንም አንስተዋል። ተመላሽ ስደተኖችን መንግስታት እንዲቀባላቸው ለማድረግም ኮሚሽኑ የዲፕሎማሲ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ወይዘሮ ቮን ዴር ላይን የደንበር ጥበቃው በአየርና ባህር ኃይል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል። ከዚሁ ጋርም በትክክል ተገን ለሚያስፈልጋቸው ከለላ እንደሚሰጥና ሰዎች በህጋዊ ቪዛ ወደ አውሮፓ የሚገቡባቸው አሰራሮችም እንደሚዘረጉ፤ እንዲሁም በቅርቡ ከቱኒዚይ ጋር ስደተኖች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ ለመቆጣጠር የተደረሰው የ105 ሚሊዮን ይሮ ፕሮጀክትም ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቀዋል።የአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና የስደተኞች ጉዳይ
ይሁን እንጂ የኮሚሽኑ እቅድ ተግባራዊነት በእጅጉ አጠራጣሪ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፤ ስደተኞችን ከጣሊያን ወደ ሌሎች አባል ገሮች እንዲዛወሩ ይደረጋል ይበሉ እንጂ በዚህ በኩል የአባል የአገሮች ስምምነት እንደሌለ ነው የሚታወቀው። ስደተኖች በህገ ወጥ መንገድ በባህር እንዳይገቡ በአየርና በባህር ጭምር ቁጥጥር እንደሚደረግ የቀረበው ዕቅድም እንዲሁ ተግባራዊነቱ አሻሚ መሆኑ የሚነገር ሲሆን፤ በዚህ ላይ ማብራሪያ የተጠየቁት የኮሚሽኑ ቃል ቀብይ ወይዘሪት አኒታ ሂፐር፤ “የደንበር ቍጥጥር ስራችንን በባህርም በአየርም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ሌሎች አማርጮችንም እናያለን” ከማለት ውጭ ብዙም አላብራሩም።
በሌላ በኩል የመብት ድርጅቶች፤ የወይዘሮ ፎን ዴር ላይንን እቅድ የስደተኖችን መብት የሚገፍና የአውሮፓ ህብረትም የተቀበላቸውን ዓለማቀፍ የስደተኖች መብት ድንጋጌዎችን የሚጥስ ነው በማለት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። ኢሮሜድራይትስ የተባለ በስደተኖች መብት ላይ የሚሰራ ድርጅት ተወካይ ወይዘሪት ሳራ ፕሪስቲያኒ ለመገናኝ ብዙኃን፤ “ የስደተኖችን የተገን ጥያቄ ሂደት ማፋጠን የሚለው አሳስቢም ነው ምክኒያቱም ስድተኛው አቤቱታው ሳይሰማ በጥድፊያ ተገን እንዲከለከል ሊያደረገው ይችላል” በማለት ይህም የጅኔቫን የስደተኞችን የመሰማትና ተገን የማግኘት መብት የሚጥስ ሊሆን ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።የጀርመን የድንበር ቁጥጥር ውሳኔ
በዋናነት በስደተኖች አጀንዳ ወደ ስልጣን የመጡት ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒ ግን ህብረቱ እወስደዋለሁ ከሚለው እርምጃ በተጨማሪ የበኩላቸውን ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በትናንትናው የካቢኔ ስብሰባቸውም ተጨማሪ የእስር ቤቶችና የተመላሽ ስደተኖች ማቆያ ማዕከሎች ግምባታ ዋና አጀንዳ እንደነበር ተገልጿል.
የአውሮፓ ህብረት በስደተኞች ጉዳይየ አስካሁን አንድ ወጥ አሰርራር ሊዘረጋና የጋር ፖሊስ ሊቀርጽ እንዳልቻለ የሚታወቅ ሲሆን፤ አጀንዳውም በአባል አገሮች መከካከል በተለይም የስደተኞች መዳረሻ በሆኑት እንደጣሊያንና ግሪክ በመሳሰሉት አገሮችና በስሜንና ምራብ ባሉ የህብረቱ አገሮች መክከል ዋና የልዩነትና የውዝግብ አጀንዳ ሆኖ እንደዘለቀ ነው።
ገበያው ንጉሤ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ